መጽሐፈ ሲራክ 9
9
ስለ ሴቶች የተሰጠ ምክር
1ክፉ ትምህርትን እንዳትማርብህ፥
ባጠገብህ የምተተኛ ሚስትህን አታስቀናት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሚስትህ ላይ አትቅና” ይላል።
2ኀይልህን እንዳታደክምብህ፥
ለሴት ልብህን አትስጣት።
3በወጥመድዋ እንዳትያዝ
የሌላ ሚስት#ግሪኩ “ወደ አመንዝራ ሴት አትሒድ” ይላል። አታባብል።
4በዘፈኗ እንዳታስትህ
ከዘፋኝ ሴት ጋር አትጫወት።
5ፈቃዷ እንዳያስትህ
ድንግልን አትቈንጥጣት።#ግሪኩ “እንዳትሰነካከልና በእርስዋ ምክንያት ቅጣት እንዳያገኝህ ድንግልን አትኵረህ አትመልከት” ይላል።
6ርስትህን እንዳታጣ
ለአመንዝራ ልቡናህን አትስጣት።
7በከተማዎቹ መንገድ ዙሪያ አታማትር፤
አደባባይዋም አያስትህ።
8ከመልከ መልካም ሴት ዐይንህን መልስ፤
የሌላ ሚስትም ደም ግባትዋ አያስጐምጅህ፤
በሴት ደም ግባት የሳቱ ሰዎች ብዙዎች ናቸውና፤
ስለዚህ ነገር ፍቅሯ እንደ እሳት ይነድዳል።
9ከጐልማሳ ሚስት ጋር አትቀመጥ፤
ልቡናህን ወደ እርሷ እንዳትወስድ፥
ሰውነትህንም በሞት እንዳታሰነካክል በመጠጥ ጊዜ ከእርሷ ጋር አትቀመጥ።
10ድንገተኛ ወዳጅ እንደ እርሱ አይሆንህምና፥
የቀድሞ ወዳጅህን አትተወው።
አዲስ ወዳጅ ጉሽ ጠጅ ነው፤
ቢከርም ግን ደስ ብሎህ ትጠጣዋለህ።
11እንደሚጠፉ አታውቅምና
የኃጥኣን ብልጽግናቸው አያስቀናህ።
12የክፉዎች ሰዎችም ተድላቸው አያስጐምጅህ፤
እስኪሞቱም ድረስ እንደማይከብሩ ዐስብ።
13በሞት ከሚቀጡ መኳንንት ፈጽመህ ራቅ፤
ሰውነትህን እንዳታጠፋ የሞት ጥርጥር አያግኝህ፥
ነገር ግን በወጥመድ መካከል እንደምትሄድ፥
በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ።
14የተቻለህን ያህል ለባልንጀራህ መልካም አድርግለት፤
ከጠቢባንም ጋር ተማከር።
15ጉዳይህም ከዐዋቂዎች ጋር ይሁን፤
ነገርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ ይሁንልህ።
16ድሆች ሰዎች በምሳሕ ጊዜ ይኑሩ፤
ክብርህም እግዚአብሔርን በመፍራት ይሁን።
17ሥራው በብልሃተኛው እጅ ይከናወናል፤
የአሕዛብንም አለቃ በቃሉ ጥበብ ያመሰግኑታል።
18ተናጋሪ ሰው በከተማው አስፈሪ ነው፥
ከቃሉም የተነሣ ፈጽሞ ይጠላል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 9: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ሲራክ 9
9
ስለ ሴቶች የተሰጠ ምክር
1ክፉ ትምህርትን እንዳትማርብህ፥
ባጠገብህ የምተተኛ ሚስትህን አታስቀናት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሚስትህ ላይ አትቅና” ይላል።
2ኀይልህን እንዳታደክምብህ፥
ለሴት ልብህን አትስጣት።
3በወጥመድዋ እንዳትያዝ
የሌላ ሚስት#ግሪኩ “ወደ አመንዝራ ሴት አትሒድ” ይላል። አታባብል።
4በዘፈኗ እንዳታስትህ
ከዘፋኝ ሴት ጋር አትጫወት።
5ፈቃዷ እንዳያስትህ
ድንግልን አትቈንጥጣት።#ግሪኩ “እንዳትሰነካከልና በእርስዋ ምክንያት ቅጣት እንዳያገኝህ ድንግልን አትኵረህ አትመልከት” ይላል።
6ርስትህን እንዳታጣ
ለአመንዝራ ልቡናህን አትስጣት።
7በከተማዎቹ መንገድ ዙሪያ አታማትር፤
አደባባይዋም አያስትህ።
8ከመልከ መልካም ሴት ዐይንህን መልስ፤
የሌላ ሚስትም ደም ግባትዋ አያስጐምጅህ፤
በሴት ደም ግባት የሳቱ ሰዎች ብዙዎች ናቸውና፤
ስለዚህ ነገር ፍቅሯ እንደ እሳት ይነድዳል።
9ከጐልማሳ ሚስት ጋር አትቀመጥ፤
ልቡናህን ወደ እርሷ እንዳትወስድ፥
ሰውነትህንም በሞት እንዳታሰነካክል በመጠጥ ጊዜ ከእርሷ ጋር አትቀመጥ።
10ድንገተኛ ወዳጅ እንደ እርሱ አይሆንህምና፥
የቀድሞ ወዳጅህን አትተወው።
አዲስ ወዳጅ ጉሽ ጠጅ ነው፤
ቢከርም ግን ደስ ብሎህ ትጠጣዋለህ።
11እንደሚጠፉ አታውቅምና
የኃጥኣን ብልጽግናቸው አያስቀናህ።
12የክፉዎች ሰዎችም ተድላቸው አያስጐምጅህ፤
እስኪሞቱም ድረስ እንደማይከብሩ ዐስብ።
13በሞት ከሚቀጡ መኳንንት ፈጽመህ ራቅ፤
ሰውነትህን እንዳታጠፋ የሞት ጥርጥር አያግኝህ፥
ነገር ግን በወጥመድ መካከል እንደምትሄድ፥
በገደልም መካከል እንደምትመላለስ ዕወቅ።
14የተቻለህን ያህል ለባልንጀራህ መልካም አድርግለት፤
ከጠቢባንም ጋር ተማከር።
15ጉዳይህም ከዐዋቂዎች ጋር ይሁን፤
ነገርህ ሁሉ በእግዚአብሔር ሕግ ይሁንልህ።
16ድሆች ሰዎች በምሳሕ ጊዜ ይኑሩ፤
ክብርህም እግዚአብሔርን በመፍራት ይሁን።
17ሥራው በብልሃተኛው እጅ ይከናወናል፤
የአሕዛብንም አለቃ በቃሉ ጥበብ ያመሰግኑታል።
18ተናጋሪ ሰው በከተማው አስፈሪ ነው፥
ከቃሉም የተነሣ ፈጽሞ ይጠላል።