መጽ​ሐፈ ሲራክ 9

9
ስለ ሴቶች የተ​ሰጠ ምክር
1ክፉ ትም​ህ​ር​ትን እን​ዳ​ት​ማ​ር​ብህ፥
ባጠ​ገ​ብህ የም​ተ​ተኛ ሚስ​ት​ህን አታ​ስ​ቀ​ናት።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “በሚ​ስ​ትህ ላይ አት​ቅና” ይላል።
2ኀይ​ል​ህን እን​ዳ​ታ​ደ​ክ​ም​ብህ፥
ለሴት ልብ​ህን አት​ስ​ጣት።
3በወ​ጥ​መ​ድዋ እን​ዳ​ት​ያዝ
የሌላ ሚስት#ግሪኩ “ወደ አመ​ን​ዝራ ሴት አት​ሒድ” ይላል። አታ​ባ​ብል።
4በዘ​ፈኗ እን​ዳ​ታ​ስ​ትህ
ከዘ​ፋኝ ሴት ጋር አት​ጫ​ወት።
5ፈቃዷ እን​ዳ​ያ​ስ​ትህ
ድን​ግ​ልን አት​ቈ​ን​ጥ​ጣት።#ግሪኩ “እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከ​ልና በእ​ር​ስዋ ምክ​ን​ያት ቅጣት እን​ዳ​ያ​ገ​ኝህ ድን​ግ​ልን አት​ኵ​ረህ አት​መ​ል​ከት” ይላል።
6ርስ​ት​ህን እን​ዳ​ታጣ
ለአ​መ​ን​ዝራ ልቡ​ና​ህን አት​ስ​ጣት።
7በከ​ተ​ማ​ዎቹ መን​ገድ ዙሪያ አታ​ማ​ትር፤
አደ​ባ​ባ​ይ​ዋም አያ​ስ​ትህ።
8ከመ​ልከ መል​ካም ሴት ዐይ​ን​ህን መልስ፤
የሌላ ሚስ​ትም ደም ግባ​ትዋ አያ​ስ​ጐ​ም​ጅህ፤
በሴት ደም ግባት የሳቱ ሰዎች ብዙ​ዎች ናቸ​ውና፤
ስለ​ዚህ ነገር ፍቅሯ እንደ እሳት ይነ​ድ​ዳል።
9ከጐ​ል​ማሳ ሚስት ጋር አት​ቀ​መጥ፤
ልቡ​ና​ህን ወደ እርሷ እን​ዳ​ት​ወ​ስድ፥
ሰው​ነ​ት​ህ​ንም በሞት እን​ዳ​ታ​ሰ​ነ​ካ​ክል በመ​ጠጥ ጊዜ ከእ​ርሷ ጋር አት​ቀ​መጥ።
10ድን​ገ​ተኛ ወዳጅ እንደ እርሱ አይ​ሆ​ን​ህ​ምና፥
የቀ​ድሞ ወዳ​ጅ​ህን አት​ተ​ወው።
አዲስ ወዳጅ ጉሽ ጠጅ ነው፤
ቢከ​ርም ግን ደስ ብሎህ ትጠ​ጣ​ዋ​ለህ።
11እን​ደ​ሚ​ጠፉ አታ​ው​ቅ​ምና
የኃ​ጥ​ኣን ብል​ጽ​ግ​ና​ቸው አያ​ስ​ቀ​ናህ።
12የክ​ፉ​ዎች ሰዎ​ችም ተድ​ላ​ቸው አያ​ስ​ጐ​ም​ጅህ፤
እስ​ኪ​ሞ​ቱም ድረስ እን​ደ​ማ​ይ​ከ​ብሩ ዐስብ።
13በሞት ከሚ​ቀጡ መኳ​ን​ንት ፈጽ​መህ ራቅ፤
ሰው​ነ​ት​ህን እን​ዳ​ታ​ጠፋ የሞት ጥር​ጥር አያ​ግ​ኝህ፥
ነገር ግን በወ​ጥ​መድ መካ​ከል እን​ደ​ም​ት​ሄድ፥
በገ​ደ​ልም መካ​ከል እን​ደ​ም​ት​መ​ላ​ለስ ዕወቅ።
14የተ​ቻ​ለ​ህን ያህል ለባ​ል​ን​ጀ​ራህ መል​ካም አድ​ር​ግ​ለት፤
ከጠ​ቢ​ባ​ንም ጋር ተማ​ከር።
15ጉዳ​ይ​ህም ከዐ​ዋ​ቂ​ዎች ጋር ይሁን፤
ነገ​ርህ ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ይሁ​ን​ልህ።
16ድሆች ሰዎች በም​ሳሕ ጊዜ ይኑሩ፤
ክብ​ር​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በመ​ፍ​ራት ይሁን።
17ሥራው በብ​ል​ሃ​ተ​ኛው እጅ ይከ​ና​ወ​ናል፤
የአ​ሕ​ዛ​ብ​ንም አለቃ በቃሉ ጥበብ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።
18ተና​ጋሪ ሰው በከ​ተ​ማው አስ​ፈሪ ነው፥
ከቃ​ሉም የተ​ነሣ ፈጽሞ ይጠ​ላል።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ