ወደ ሮሜ ሰዎች 9:10-15

ወደ ሮሜ ሰዎች 9:10-15 አማ2000

ነገር ግን ለእ​ር​ስዋ ብቻ አይ​ደ​ለም፤ ርብ​ቃም ለአ​ባ​ታ​ችን ለይ​ስ​ሐቅ መንታ በፀ​ነ​ሰች ጊዜ፥ ሳይ​ወ​ለዱ፥ ክፉና መል​ካም ሥራም ሳይ​ሠሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መም​ረጡ በምን እንደ ሆነ ይታ​ወቅ ዘንድ፥ እርሱ የጠ​ራው ነው እንጂ ሰው በሥ​ራው የሚ​መ​ረጥ አን​ዳ​ይ​ደ​ለም ያውቁ ዘንድ፥ ለር​ብቃ፥ “ታላቁ ለታ​ናሹ ይገ​ዛል” አላት። “ያዕ​ቆ​ብን ወደ​ድሁ፤ ዔሳ​ውን ግን ጠላሁ” ተብሎ እን​ዲሁ ተጽ​ፎ​አ​ልና። እን​ግ​ዲህ ምን እን​ላ​ለን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያደ​ላ​ልን? አያ​ደ​ላም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ አለው፥ “የም​ም​ረ​ውን እም​ረ​ዋ​ለሁ፤ ይቅር የም​ለ​ው​ንም ይቅር እለ​ዋ​ለሁ።”