እንደ ሥጋ ፈቃድ የሚኖሩ የሥጋን ነገር ያስባሉና፤ እንደ መንፈስ ፈቃድ የሚኖሩ ግን የመንፈስን ነገር ያስባሉ። የሥጋ ዐሳብ ሞትን ያመጣብናል፤ የመንፈስ ዐሳብ ግን ሰላምንና ሕይወትን ይሰጠናል። የሥጋ ዐሳብ ለእግዚአብሔር ጠላቱ ነውና፤ ለእግዚአብሔርም ሕግ ስለማይገዛ፥ መፈጸም አይቻለውም። ለሥጋዊ ፈቃዳቸው የሚሠሩ ሁሉ እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይችሉም። እናንተ ግን ለመንፈሳዊ ሕግ እንጂ ለሥጋችሁ ፈቃድ የምትሠሩ አይደላችሁም፤ የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ አድሮ ይኖራልና፤ የክርስቶስ መንፈስ ያላደረበት ግን እርሱ የእርሱ ወገን አይደለም። ክርስቶስ ካደረባችሁ ግን ሰውነታችሁን ከኀጢአት ሥራ ለዩ፤ መንፈሳችሁንም ለጽድቅ ሥራ ሕያው አድርጉ። ጌታችን ኢየሱስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው የእግዚአብሔር መንፈስ ካደረባችሁ ኢየሱስ ክርስቶስን ከሙታን ለይቶ ያስነሣው እርሱ አድሮባችሁ ባለ መንፈሱ ለሟች ሰውነታችሁ ሕይወትን ይሰጣታል። ወንድሞቻችን፥ አሁንም በሥጋችን ሳለን በሥጋ ፈቃድ እንኖር ዘንድ አይገባም። እንደ ሥጋ ፈቃድ ብትኖሩ ትሞታላችሁ፤ ነገር ግን በመንፈሳዊ ሥራ የሥጋችሁን ፈቃድ ብትገድሉ ለዘለዓለም በሕይወት ትኖራላችሁ። በእግዚአብሔር መንፈስ የሚሠሩ ሁሉ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው።
ወደ ሮሜ ሰዎች 8 ያንብቡ
ያዳምጡ ወደ ሮሜ ሰዎች 8
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ወደ ሮሜ ሰዎች 8:5-14
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች