ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5-13

ወደ ሮሜ ሰዎች 2:5-13 አማ2000

ነገር ግን ልቡ​ና​ህን እንደ ማጽ​ና​ትህ፥ ንስ​ሓም እንደ አለ​መ​ግ​ባ​ትህ መጠን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እው​ነ​ተና ፍርድ በሚ​ገ​ለ​ጥ​በት ቀን መቅ​ሠ​ፍ​ትን ለራ​ስህ ታከ​ማ​ቻ​ለህ። እርሱ በእ​ው​ነ​ተና ፍርዱ ለሁሉ እንደ ሥራው ይከ​ፍ​ለ​ዋ​ልና። በበጎ ምግ​ባር ጸን​ተው ለሚ​ታ​ገሡ፥ ምስ​ጋ​ናና ክብ​ርን፥ የማ​ይ​ጠፋ ሕይ​ወ​ት​ንም ለሚሹ እርሱ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ይሰ​ጣ​ቸ​ዋል። ለሚ​ክ​ዱና እው​ነ​ትን ለሚ​ለ​ውጡ፥ ዐመ​ፅ​ንም ለሚ​ወ​ድዱ ሰዎች ዋጋ​ቸው ቍጣና መቅ​ሠ​ፍት ነው። መከ​ራና ጭን​ቀት አስ​ቀ​ድሞ በአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም በአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ ክፉ በሆነ ሰው ሁሉ ላይ ነው። ምስ​ጋ​ናና ክብር፥ ሰላ​ምም አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ይ​ሁ​ዳዊ፥ ደግ​ሞም ለአ​ረ​ማዊ፥ ሥራዉ መል​ካም ለሆነ ሁሉ ነው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሰው ፊት አያ​ዳ​ላ​ምና። ከሕግ ወጥ​ተው የበ​ደሉ በሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል፤ ያለ ሕግ የበ​ደሉ ሁሉም ያለ ሕግ ይፈ​ረ​ድ​ባ​ቸ​ዋል። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ሕግን የሚ​ያ​ደ​ርጉ ይጸ​ድ​ቃሉ እንጂ ሕግን የሚ​ሰሙ አይ​ጸ​ድ​ቁ​ምና።