ማቅ ለበስሁ መተረቻም ሆንሁላቸው። በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፤ ወይን የሚጠጡም በእኔ ይዘፍናሉ። እኔስ በጸሎቴ ወደ እግዚአብሔር ነኝ የእግዚአብሔር ይቅርታው በጊዜው ነው፤ ይቅርታህ ብዙ ሲሆን መድኃኒቴ ሆይ፥ በእውነት አድነኝ። እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፤ ከጠላቶችና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ። የውኃ ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጕድጓዶችም አፋቸውን በኔ ላይ አይክፈቱ፤ አቤቱ፥ ምሕረትህ መልካም ናትና ስማኝ፤ እንደ ይቅርታህም ብዛት ወደ እኔ ተመልከት፤ ከባሪያህም ፊትህን አትመልስ፤ ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ ስማኝ። ነፍሴን ተመልክተህ ተቤዣት፤ ስለ ጠላቶችም አድነኝ። አንተ ስድቤን፥ እፍረቴንም፥ ነውሬንም ታውቃለህ፤ በሚያስጨንቁኝ ሁሉ ፊት። ሰውነቴ ስድብንና ውርደትን ታገሠች፤ አዝኜ ተቀመጥሁ፥ የሚያጽናናኝም አጣሁ።
መዝሙረ ዳዊት 68 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መዝሙረ ዳዊት 68:11-20
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች