መዝ​ሙረ ዳዊት 20:1-9

መዝ​ሙረ ዳዊት 20:1-9 አማ2000

አቤቱ፥ በኀ​ይ​ልህ ንጉሥ ደስ ይለ​ዋል፤ በማ​ዳ​ን​ህም እጅግ ሐሤ​ትን ያደ​ር​ጋል። የል​ቡን ፈቃድ ሰጠ​ኸው፥ የከ​ን​ፈ​ሮ​ቹ​ንም ልመና አል​ከ​ለ​ከ​ል​ኸ​ውም። በበጎ በረ​ከት ደር​ሰ​ህ​ለ​ታ​ልና፤ ከክ​ቡር ዕንቍ የሆነ ዘው​ድ​ንም በራሱ ላይ አኖ​ርህ። ሕይ​ወ​ትን ለመ​ነህ፥ ሰጠ​ኸ​ውም፥ ለረ​ዥም ዘመን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ። በማ​ዳ​ንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ጨመ​ር​ህ​ለት። የዘ​ለ​ዓ​ለም በረ​ከ​ትን ሰጥ​ተ​ኸ​ዋ​ልና፥ በፊ​ት​ህም ደስታ ደስ ታሰ​ኘ​ዋ​ለህ። ንጉሥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተማ​ም​ኖ​አ​ልና፥ በል​ዑ​ልም ምሕ​ረት አይ​ና​ወ​ጥም። እጅህ ጠላ​ቶ​ች​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው፥ ቀኝ​ህም የሚ​ጠ​ሉ​ህን ሁሉ ታግ​ኛ​ቸው። ፊትህ በተ​ቈጣ ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድ​ር​ጋ​ቸው፤ አቤቱ፥ በቍ​ጣህ አው​ካ​ቸው፥ እሳ​ትም ትብ​ላ​ቸው።