መዝ​ሙረ ዳዊት 15:1-5

መዝ​ሙረ ዳዊት 15:1-5 አማ2000

አቤቱ፥ በአ​ንተ ታም​ኛ​ለ​ሁና ጠብ​ቀኝ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ በጎ​ነ​ቴን አት​ሻ​ት​ምና። ፈቃ​ድህ ሁሉ በም​ድር ባሉት ቅዱ​ሳን ላይ ተገ​ለጠ። ደዌ​ያ​ቸው በዛ፤ ከዚ​ያም በኋላ ተፋ​ጠኑ፤ በደም ማኅ​በ​ራ​ቸው አል​ተ​ባ​በ​ርም። ስማ​ቸ​ው​ንም በአፌ አል​ጠ​ራም። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የር​ስቴ ዕድል ፋን​ታና ጽዋዬ ነው፥ ርስ​ቴን የም​ት​መ​ልስ አንተ ነህ።