መዝ​ሙረ ዳዊት 139:5-10

መዝ​ሙረ ዳዊት 139:5-10 አማ2000

ትዕ​ቢ​ተ​ኞች ወጥ​መ​ድን ሰወ​ሩ​ብኝ፥ ለእ​ግ​ሮ​ቼም የወ​ጥ​መድ ገመ​ድን ዘረጉ፤ በመ​ን​ገ​ዴም ዕን​ቅ​ፋ​ትን አኖሩ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም፥ “አንተ አም​ላኬ ነህ፤ የል​መ​ና​ዬን ቃል፥ አቤቱ፥ አድ​ምጥ” አል​ሁት። አቤቱ፥ ጌታዬ፥ የድ​ኅ​ነቴ ኀይል፥ በጦ​ር​ነት ቀን በራሴ ላይ ሁነህ ሰወ​ር​ኸኝ። አቤቱ፥ ጌታዬ፥ ከም​ኞቴ የተ​ነሣ ለኀ​ጢ​አ​ተ​ኞች አት​ስ​ጠኝ፤ በላዬ ተማ​ከሩ፥ እን​ዳ​ይ​ታ​በ​ዩም አት​ተ​ወኝ። የአ​ሽ​ክ​ላ​ቸው ራስ የከ​ን​ፈ​ራ​ቸ​ውም ክፋት ይድ​ፈ​ና​ቸው። የእ​ሳት ፍም በላ​ያ​ቸው ይው​ደቅ፤ መቆም እን​ዳ​ይ​ችሉ በች​ግር ወደ ምድር ይው​ደቁ።