መዝ​ሙረ ዳዊት 109:1-4

መዝ​ሙረ ዳዊት 109:1-4 አማ2000

ጌታ ጌታ​ዬን፥ “ጠላ​ቶ​ች​ህን ለእ​ግ​ርህ መረ​ገጫ እስ​ካ​ደ​ር​ግ​ልህ ድረስ በቀኜ ተቀ​መጥ” አለው። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ይ​ልን በትር ከጽ​ዮን ይል​ክ​ል​ሃል፤ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህም መካ​ከል ትገ​ዛ​ለህ። ቀዳ​ማዊ፦ በኀ​ይል ቀን፥ በቅ​ዱ​ሳን ብር​ሃን ከአ​ንተ ጋር ነበር፥ ከአ​ጥ​ቢያ ኮከብ አስ​ቀ​ድሞ ከሆድ ወለ​ድ​ሁህ። እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት አንተ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ካህን ነህ ብሎ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማለ አይ​ጸ​ጸ​ት​ምም።