መዝሙር 109:1-4

መዝሙር 109:1-4 NASV

የምስጋናዬ ምንጭ የሆንህ አምላክ ሆይ፤ ዝም አትበል፤ ክፉዎችና አታላዮች፣ አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤ በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል። በጥላቻ ቃል ከብበውኛል፤ ያለ ምክንያትም ጥቃት አድርሰውብኛል። ስወድዳቸው ይወነጅሉኛል፤ እኔ ግን እጸልያለሁ።