ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 4:1-5

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 4:1-5 አማ2000

አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ች​ሁና የም​ና​ፍ​ቃ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ደስ​ታ​ች​ንና አክ​ሊ​ላ​ችን ናችሁ፤ ወዳ​ጆ​ቻ​ችን ሆይ፥ እን​ዲህ ቁሙ፤ በጌ​ታ​ች​ንም ጽኑ። ኤዎ​ድ​ያና ስን​ጣ​ክን ሆይ፥ በአ​ንድ ልብ ጌታ​ች​ንን ለማ​ገ​ል​ገል ታስቡ ዘንድ እማ​ል​ዳ​ች​ኋ​ለሁ። ወን​ድ​ሜና አጋዤ ስት​ሪካ ሆይ፥ እን​ድ​ት​ረ​ዳ​ቸው አን​ተ​ንም እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ፤ ወን​ጌ​ልን በማ​ስ​ተ​ማር ከቀ​ሌ​ም​ን​ጦ​ስና ሥራ​ቸው ከተ​ባ​በረ፥ ስማ​ቸ​ውም በሕ​ይ​ወት መጽ​ሐፍ ከተ​ጻ​ፈ​ላ​ቸው ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ንም ሁሉ ጋር ከእ​ኔም ጋር ደክ​መ​ዋ​ልና። ዘወ​ትር በጌ​ታ​ችን ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ደግሜ እላ​ች​ኋ​ለሁ፦ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ፍጹ​ም​ነ​ታ​ች​ሁም በሰው ሁሉ ዘንድ ይታ​ወቅ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅርብ ነው፤