ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 2:9-18

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 2:9-18 አማ2000

ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ከስም ሁሉ የሚ​በ​ልጥ ስም​ንም ሰጠው። ይህም በሰ​ማ​ይና በም​ድር በቀ​ላ​ያ​ትና ከም​ድር በታች ያለ ጕል​በት ሁሉ ለኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ስም ይሰ​ግድ ዘንድ ነው። አን​ደ​በ​ትም ሁሉ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አብ ክብር ጌታ እንደ ሆነ ያምን ዘንድ ነው። አሁ​ንም ወን​ድ​ሞች ሆይ፥ ዘወ​ትር እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይ​ሆን፥ ሳል​ኖ​ርም በፍ​ር​ሀ​ትና በመ​ን​ቀ​ጥ​ቀጥ ሆና​ችሁ ለድ​ኅ​ነ​ታ​ችሁ ሥሩ። ለሚ​ወ​ደው ሥራ የሚ​ረ​ዳ​ችሁ እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታ​ውን ይፈ​ጽ​ም​ላ​ችሁ። የም​ት​ሠ​ሩ​ትን ሁሉ ያለ ማን​ጐ​ራ​ጐ​ርና ያለ መጠ​ራ​ጠር በፍ​ቅ​ርና በስ​ም​ም​ነት ሥሩ። እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጆች ንጹ​ሓ​ንና የዋ​ሃን ትሆኑ ዘንድ፥ በማ​ያ​ም​ኑና በጠ​ማ​ሞች ልጆች መካ​ከል ነውር ሳይ​ኖ​ር​ባ​ችሁ በዓ​ለም እንደ ብር​ሃን ትታ​ያ​ላ​ችሁ፤ የሕ​ይ​ወ​ትን ቃል እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ችሁ፤ ክር​ስ​ቶስ በሚ​መ​ጣ​በት ቀን እኔ እን​ድ​መካ፤ የሮ​ጥሁ በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና፤ የደ​ከ​ም​ሁም በከ​ንቱ አይ​ደ​ለ​ምና። ስለ ሃይ​ማ​ኖ​ታ​ች​ሁም የአ​ም​ልኮ መሥ​ዋ​ዕ​ትን እሠ​ዋ​ለሁ። እነ​ሆም እኔ በእ​ና​ንተ ደስ ይለ​ኛል፤ እና​ን​ተም በእኔ ደስ ይበ​ላ​ችሁ። ከእ​ኔም ጋር ሐሤት አድ​ርጉ።