ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 2:5-9

ወደ ፊል​ጵ​ስ​ዩስ ሰዎች 2:5-9 አማ2000

ፍጹ​ማን የሆ​ና​ችሁ ሁላ​ችሁ ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ለእኛ እንደ አደ​ረ​ገ​ልን ይህን አስቡ። ይኸ​ውም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መልኩ ነው፤ ቀምቶ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሆነ አይ​ደ​ለም። ነገር ግን የባ​ር​ያን መልክ ይዞ፥ በሰ​ውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ዝቅ አደ​ረገ። እንደ ሰውም ሆኖ ራሱን አዋ​ረደ፤ ለሞት እስከ መድ​ረ​ስም ታዘዘ፤ ሞቱም በመ​ስ​ቀል የሆ​ነው ነው። ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅግ ከፍ ከፍ አደ​ረ​ገው፤ ከስም ሁሉ የሚ​በ​ልጥ ስም​ንም ሰጠው።