ኦሪት ዘኍ​ልቍ 21:1-3

ኦሪት ዘኍ​ልቍ 21:1-3 አማ2000

በአ​ዜብ በኩል ተቀ​ምጦ የነ​በ​ረው ከነ​ዓ​ና​ዊው የአ​ራድ ንጉሥ በአ​ታ​ሪን መን​ገድ እስ​ራ​ኤል እንደ መጡ ሰማ፤ ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ጋር ሰልፍ አደ​ረገ ከእ​ነ​ር​ሱም ምርኮ ማረከ። እስ​ራ​ኤ​ልም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ይህን ሕዝብ አሳ​ል​ፈህ በእ​ጃ​ችን ብት​ሰ​ጠን እር​ሱ​ንና ከተ​ሞ​ቹን ሕርም ብለን እና​ጠ​ፋ​ዋ​ለን” ብለው ስእ​ለት ተሳሉ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ድምፅ ሰማ፤ ከነ​ዓ​ና​ው​ያ​ን​ንም አሳ​ልፎ በእ​ጃ​ቸው ሰጣ​ቸው፤ እነ​ር​ሱ​ንም፥ ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ሕርም ብለው አጠ​ፉ​አ​ቸው፤ የዚ​ያን ስፍራ ስም “ሕርም” ብለው ጠሩት።