የሉቃስ ወንጌል 6:43-46
የሉቃስ ወንጌል 6:43-46 አማ2000
ክፉ ፍሬን የሚያፈራ መልካም ዛፍ የለም፤ መልካም ፍሬ የሚያፈራ ክፉ ዛፍም የለም። ዛፍ ሁሉ ከፍሬው ይታወቃል፤ ከእሾህ በለስን አይለቅሙም፤ ከደንደርም ወይንን አይለቅሙም። መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካምን ያወጣል፤ ክፉ ሰውም ከልቡ ክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል፤ ከልብ የተረፈውን አፍ ይናገራልና። “ለምን አቤቱ፥ አቤቱ፥ ትሉኛላችሁ? የምላችሁንም አታደርጉም።

