ሄ። እግዚአብሔር እንደ ጠላት ሆነብኝ፤ እስራኤልን አሰጠመ። አዳራሾችዋን ሁሉ ዋጠ፤ አንባዎችዋንም አጠፋ። በይሁዳም ሴት ልጅ ውርደትንና ጕስቍልናን አበዛ። ዋው። ማደሪያውን እንደ ወይን ጋረደ፤ በዓሉን ሁሉ አጠፋ፤ እግዚአብሔር በጽዮን ያደረገውን በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፤ በቍጣውም መዓት ነገሥታቱን፥ አለቆቹንና ካህናቱን አጠፋ። ዛይ። እግዚአብሔር መሠዊያውን ጣለ፤ መቅደሱንም ጠላው፤ የአዳራሾችዋንም ቅጥር በጠላት እጅ ሰበረ። እንደ ዓመት በዓል ቀን በእግዚአብሔር ቤት ድምፃቸውን በዕልልታ አሰሙ። ሔት። እግዚአብሔር የጽዮንን ሴት ልጅ ቅጥር ያፈርስ ዘንድ ዐሰበ፤ የመለኪያውንም ገመድ ዘረጋ፤ እርስዋን ከማጥፋት እጁን አልመለሰም፤ ምሽጉና ቅጥሩ አለቀሱ፤ በአንድነትም ደከሙ። ጤት። በሮችዋ በመሬት ውስጥ ሰጠሙ፤ መወርወሪያዎችዋም ተሰበሩ፤ ንጉሥዋና አለቃዋ በአሕዛብ መካከል አሉ፤ ሕግም የለም። ነቢያቷም ከእግዚአብሔር ዘንድ ራእይ አላዩም። ዮድ። የጽዮን ሴት ልጅ ሽማግሌዎች ዝም ብለው በመሬት ላይ ተቀምጠዋል፤ ትቢያን በራሳቸው ላይ ነሰነሱ፤ ማቅም ታጠቁ፤ በኢየሩሳሌም መሳፍንቱንና ደናግሉን ወደ ምድር አወረዷቸው። ካፍ። ሕፃኑና ጡት የሚጠባው በከተማዪቱ ጎዳና ላይ ሲዝሉ፥ ዐይኔ በእንባ ደከመች፤ ልቤም ታወከ፤ ስለ ወገኔ ሴት ልጅ መከራ ክብሬ በምድር ላይ ተዋረደ። ላሜድ። በከተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፥ “እህልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉአቸዋል። ሜም። የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፥ ምን እመሰክርልሻለሁ? በምንስ እመስልሻለሁ? ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ማን ያድንሻል? ማንስ ያጽናናሻል? ስብራትሽ እንደ ባሕር ታላቅ ነውና፤ የሚፈውስሽ ማን ነው? ኖን። ነቢያትሽ ከንቱና ዕብደትን አይተውልሻል፤ ምርኮሽን ይመልሱ ዘንድ በደልሽን አልገለጡም፤ ከንቱና የማይረባ ነገርንም አይተውልሻል። ሳምኬት። መንገድ ዐላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻል፦ “በውኑ የምድር ሁሉ ደስታ፥ አክሊልና ክብር የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን?” እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፤ ራሳቸውንም ይነቀንቃሉ። ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፤ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፥ “ውጠናታል፤ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፤ አግኝተናታል አይተናትማል” ይላሉ። ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፤ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውንም ቃል ፈጸመ፤ አፈረሳት፤ አልራራላትምም፤ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፤ የጠላቶችሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ። ጻዴ። ልባቸው ወደ ጌታ ጮኸ፤ የጽዮን ሴት ልጅ ቅጥር ሆይ፥ እንባሽን እንደ ፈሳሽ ቀንና ሌሊት አፍስሺ፤ ለሰውነትሽ ዕረፍት አትስጪ፤ የዐይንሽንም ብሌን አታቋርጪ። ቆፍ። ተነሺ፤ በሌሊት በመጀመሪያው ሰዓት ጩኺ፥ በጌታም ፊት ልብሽን እንደ ውኃ አፍስሺ፤ በጎዳና ሁሉ ራስ ላይ በራብ ስለ ደከሙ ስለ ሕፃናትሽ ነፍስ እጆችሽን ወደ እርሱ አንሺ።
ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 2 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: ሰቆቃወ ኤርምያስ ነቢይ 2:5-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች