መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 9:3-6

መጽ​ሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 9:3-6 አማ2000

በገ​ባ​ዖን የሚ​ኖሩ ሰዎች ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በኢ​ያ​ሪ​ኮና በጋይ ያደ​ረ​ገ​ውን በሰሙ ጊዜ፥ እነ​ርሱ ደግሞ ተን​ኰል አድ​ር​ገው መጡ፤ ለራ​ሳ​ቸ​ውም ስንቅ ያዙ፤ በት​ከ​ሻ​ቸ​ውም ላይ አሮጌ ዓይ​በ​ትና ያረ​ጀና የተ​ቀ​ደደ የተ​ጠ​ቀ​መም የጠጅ ረዋት ተሸ​ከሙ። በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም ያደ​ረ​ጉት ጫማ ያረ​ጀና ማዘ​ቢ​ያው የተ​በ​ጣ​ጠሰ፥ ልብ​ሳ​ቸ​ውም በላ​ያ​ቸው ያረጀ ነበረ፤ ለስ​ን​ቅም የያ​ዙት እን​ጀራ ሁሉ የደ​ረቀ፥ የሻ​ገ​ተና የተ​በ​ላሸ ነበረ። ወደ ኢያ​ሱና ወደ እስ​ራ​ኤል ጉባኤ ወደ ጌል​ገላ መጥ​ተው ለኢ​ያ​ሱና ለእ​ስ​ራ​ኤል ሁሉ፥ “ከሩቅ ሀገር መጥ​ተ​ናል፤ አሁ​ንም ከእኛ ጋር ቃል ኪዳን አድ​ርጉ” አሉ።