ኢያሱም፥ ተዋጊዎቹም ሕዝብ ሁሉ ተነሥተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያሱም ጽኑዓን፥ ተዋጊዎችና ኀያላን የሆኑትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌሊትም ላካቸው። እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከተማዪቱ በስተኋላ ተደበቁ፤ ከከተማዪቱ አትራቁ፤ ሁላችሁም ተዘጋጅታችሁ ተቀመጡ፤ እኔ፥ ከእኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተማዪቱ እንቀርባለን፤ የጋይም ሰዎች እኛን ሊገናኙ እንደ ፊተኛው በወጡ ጊዜ ከፊታቸው እንሸሻለን፤ ወጥተውም በተከተሉን ጊዜ ከከተማ እናርቃቸዋለን፤ እነርሱም እንደ በፊቱ ከፊታችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊታቸው እንሸሻለን። እንግዲህ እናንተም ከተደበቃችሁበት ስፍራ ተነሡ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር እርስዋን በእጃችሁ አሳልፎ ይሰጣልና ከተማዪቱን ያዙ። በያዛችኋትም ጊዜ ከተማዪቱን በእሳት አቃጥሉአት፤ እንደ አልኋችሁ አድርጉ፤ እነሆ፥ አዝዣችኋለሁ።”
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 8 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 8:3-8
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች