ኢያሱ 8:3-8

ኢያሱ 8:3-8 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ኢያ​ሱም፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያ​ሱም ጽኑ​ዓን፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችና ኀያ​ላን የሆ​ኑ​ትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌ​ሊ​ትም ላካ​ቸው። እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ ተደ​በቁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ አት​ራቁ፤ ሁላ​ች​ሁም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤ እኔ፥ ከእ​ኔም ጋር ያለው ሕዝብ ሁሉ ወደ ከተ​ማ​ዪቱ እን​ቀ​ር​ባ​ለን፤ የጋ​ይም ሰዎች እኛን ሊገ​ናኙ እንደ ፊተ​ኛው በወጡ ጊዜ ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን፤ ወጥ​ተ​ውም በተ​ከ​ተ​ሉን ጊዜ ከከ​ተማ እና​ር​ቃ​ቸ​ዋ​ለን፤ እነ​ር​ሱም እንደ በፊቱ ከፊ​ታ​ችን ሸሹ ይላሉ፤ እኛም ከፊ​ታ​ቸው እን​ሸ​ሻ​ለን። እን​ግ​ዲህ እና​ን​ተም ከተ​ደ​በ​ቃ​ች​ሁ​በት ስፍራ ተነሡ፤ አም​ላ​ካ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እር​ስ​ዋን በእ​ጃ​ችሁ አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ልና ከተ​ማ​ዪ​ቱን ያዙ። በያ​ዛ​ች​ኋ​ትም ጊዜ ከተ​ማ​ዪ​ቱን በእ​ሳት አቃ​ጥ​ሉ​አት፤ እንደ አል​ኋ​ችሁ አድ​ርጉ፤ እነሆ፥ አዝ​ዣ​ች​ኋ​ለሁ።”