መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 22:1-5
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 22:1-5 አማ2000
በዚያን ጊዜም ኢያሱ የሮቤልን ልጆችና የጋድን ልጆች የምናሴንም ነገድ እኩሌታ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ሁሉ ሰምታችኋል፤ እኔም ላዘዝኋችሁ ነገር ሁሉ ታዝዛችኋል፤ ይህንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወንድሞቻችሁን አልተዋችሁም፤ የአምላካችሁንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ጠብቃችኋል። አሁንም አምላካችሁ እግዚአብሔር እንደ ተናገራቸው ወንድሞቻችሁን አሳርፎአቸዋል፤ አሁን እንግዲህ ተመለሱ፤ ወደ ቤታችሁና የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በዮርዳኖስ ማዶ ወደ ሰጣችሁ ወደ ርስታችሁ ምድር ሂዱ። ብቻ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን ታደርጉ ዘንድ፥ አምላካችሁን እግዚአብሔርንም ትወድዱ ዘንድ፥ መንገዱንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእዛዙንም ትጠብቁ ዘንድ፥ እርሱንም ትከተሉ ዘንድ፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ ታመልኩት ዘንድ እጅግ ተጠንቀቁ።”

