ኢያሱ 22:1-5

ኢያሱ 22:1-5 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

በዚ​ያን ጊዜም ኢያሱ የሮ​ቤ​ልን ልጆ​ችና የጋ​ድን ልጆች የም​ና​ሴ​ንም ነገድ እኩ​ሌታ ጠርቶ እን​ዲህ አላ​ቸው፦ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ሁሉ ሰም​ታ​ች​ኋል፤ እኔም ላዘ​ዝ​ኋ​ችሁ ነገር ሁሉ ታዝ​ዛ​ች​ኋል፤ ይህ​ንም ያህል ብዙ ጊዜ እስከ ዛሬ ድረስ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አል​ተ​ዋ​ች​ሁም፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ ጠብ​ቃ​ች​ኋል። አሁ​ንም አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተና​ገ​ራ​ቸው ወን​ድ​ሞ​ቻ​ች​ሁን አሳ​ር​ፎ​አ​ቸ​ዋል፤ አሁን እን​ግ​ዲህ ተመ​ለሱ፤ ወደ ቤታ​ች​ሁና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ማዶ ወደ ሰጣ​ችሁ ወደ ርስ​ታ​ችሁ ምድር ሂዱ። ብቻ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሕጉን ታደ​ርጉ ዘንድ፥ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ትወ​ድዱ ዘንድ፥ መን​ገ​ዱ​ንም ሁሉ ትሄዱ ዘንድ፥ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ትጠ​ብቁ ዘንድ፥ እር​ሱ​ንም ትከ​ተሉ ዘንድ፥ በፍ​ጹ​ምም ልባ​ችሁ በፍ​ጹ​ምም ነፍ​ሳ​ችሁ ታመ​ል​ኩት ዘንድ እጅግ ተጠ​ን​ቀቁ።”