የሌዊ ልጆች አለቆች ወደ ካህኑ ወደ አልዓዛር፥ ወደ ነዌም ልጅ ወደ ኢያሱ ወደ እስራኤልም ሕዝብ አባቶች ነገዶች አለቆች መጡ፤ በከነዓን ምድር ባለችው በሴሎ፥ “እግዚአብሔር በሙሴ እጅ የምንቀመጥባቸውን ከተሞች፥ ለከብቶቻችንም መሰማሪያዎች ትሰጡን ዘንድ አዝዞአል” ብለው ተናገሩአቸው። የእስራኤልም ልጆች እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ ከርስታቸው እነዚህን ከተሞችና መሰማርያቸውን ለሌዋውያን ሰጡአቸው። ለቀዓትም ወገኖች ልጆች ዕጣ ወጣ፤ ሌዋውያንም ለነበሩ ለካህኑ ለአሮን ልጆች ከይሁዳ ነገድ፥ ከስምዖንም ነገድ፥ ከብንያምም ነገድ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው። ለቀሩትም ለቀዓት ልጆች ከኤፍሬም ነገድ፥ ከዳንም ነገድ፥ ከምናሴም ነገድ እኩሌታ ዐሥር ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው። ለጌድሶንም ልጆች ከይሳኮር ነገድ፥ ከአሴርም ነገድ፥ ከንፍታሌምም ነገድ፥ በባሳንም ካለው ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ዐሥራ ሦስት ከተሞች በዕጣ ተሰጡአቸው። ለሜራሪም ልጆች በየወገኖቻቸው ከሮቤል ነገድ፥ ከጋድም ነገድ፥ ከዛብሎንም ነገድ ዐሥራ ሁለት ከተሞች ተሰጡአቸው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው የእስራኤል ልጆች እነዚህን ከተሞችና መሰማሪያቸውን ለሌዋውያን በዕጣ ሰጡ። የይሁዳም ልጆች ነገድ፥ የስምዖንም ልጆች ነገድ፥ የብንያምም ልጆች ነገድ በስማቸው የተጠሩትን እነዚህን ከተሞች ሰጡአቸው። የፊተኛው ዕጣ ለእነርሱ ስለወጣ የሌዊ ልጆች የቀዓት ወገን ለሆኑ ለአሮን ልጆች ሆኑ። የኤናቅ ልጆች ከተማ ቅርያትያርቦቅንና በዙሪያዋ ያሉ መሰማሪያዎችን ሰጡአቸው፤ ይህችውም በይሁዳ ተራራ ያለች ኬብሮን ናት። ኢያሱም የከተማዪቱን እርሻ መንደሮችዋንም ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ልጆች ርስት አድርጎ ሰጣቸው። ለካህኑም ለአሮን ልጆች እነዚህን ሰጡ፤ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ ከተማ የሆነችውን ኬብሮንንና መሰማርያዋን፤ ሌምናንና መሰማርያዋን፥ ኤቴርንና መሰማርያዋን፥ ኤታምንንና መሰማርያዋን፤ ሄሎንንና መሰማርያዋን፥ ዳቤርንና መሰማርያዋን፥ አሳንና መሰማርያዋን፥ ዮጣንንና መሰማርያዋን፥ ቤትሳሚስንና መሰማርያዋን፤ ከእነዚህ ከሁለቱ ነገዶች ዘጠኝ ከተሞችን ሰጡ። ከብንያምም ነገድ ገባዖንንና መሰማርያዋን፥ ጋቲትንና መሰማርያዋን፤ ዓናቶትንና መሰማርያዋን፥ አልሞንንና መሰማርያዋን፤ አራት ከተሞችን ሰጡ። የካህናቱ የአሮን ልጆች ከተሞች ከመሰማሪያዎቻቸው ጋር ዐሥራ ሦስት ናቸው፤
መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 21:1-19
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች