ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 48

48
ስለ ሞአብ መጥ​ፋት የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1ስለ ሞአብ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍ​ታ​ለ​ችና ወዮ​ላት! ቂር​ያ​ታ​ይም አፍ​ራ​ለች፤ ተይ​ዛ​ማ​ለች፤ መጠ​ጊ​ያ​ዋም አፍ​ራ​ለች፤ ደን​ግ​ጣ​ማ​ለች። 2ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ የሞ​አብ ፈውስ#ዕብ. “ትም​ክ​ህት” ይላል። የለም፤ በሐ​ሴ​ቦን ላይ፥ “ኑ ሕዝብ እን​ዳ​ት​ሆን እና​ጥ​ፋት” ብለው ክፉ ነገ​ርን አስ​በ​ው​ባ​ታል። ፈጽሞ ትተ​ዋ​ለች፤ ከኋ​ላዋ ሰይፍ ይመ​ጣ​ልና።#ዕብ. “መድ​ሜን ሆይ አንቺ ደግሞ ትጠ​ፊ​ያ​ለሽ ፤ ሰይ​ፍም ያሳ​ድ​ድ​ሻል” ይላል። 3መፍ​ረ​ስና ታላቅ ጥፋት የሚል የጩ​ኸት ቃል ከሖ​ሮ​ና​ይም#“ከሖ​ሮ​ና​ይም” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ተሰማ። 4ሞአብ ጠፍ​ታ​ለች፤ ይህ​ንም በሴ​ጎር ተና​ገሩ።#ዕብ. “ልጆ​ች​ዋም ጩኸ​ትን አሰ​ም​ተ​ዋል” ይላል። 5በሎ​ዊት ዓቀ​በት ልቅሶ እያ​ለ​ቀሱ ይወ​ጣ​ሉና፥ በሖ​ሮ​ና​ይ​ምም መን​ገድ የመ​ባ​ባ​ትን ጩኸት ሰም​ተ​ዋል።
6“ሸሽ​ታ​ችሁ ራሳ​ች​ሁን አድኑ፤ እንደ ሜዳ አህያ በም​ድረ በዳ ተቀ​መጡ፤ 7በሥ​ራ​ሽና በመ​ዝ​ገ​ብሽ ታም​ነ​ሻ​ልና አንቺ ደግሞ ትያ​ዢ​ያ​ለሽ፤ ካሞ​ሽም ከካ​ህ​ና​ቱና ከአ​ለ​ቆቹ ጋር በአ​ን​ድ​ነት ይማ​ረ​ካል። 8እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ተና​ገረ፥ ጥፋት ወደ ከተማ ሁሉ ይመ​ጣል፤ አን​ዲ​ትም ከተማ አት​ድ​ንም፤ ሸለ​ቆ​ውም ይጠ​ፋል፤ ሜዳ​ውም ይበ​ላ​ሻል። 9በርራ እን​ድ​ት​ወጣ ለሞ​አብ ክንፍ ስጡ​አት፤ ከተ​ሞ​ች​ዋም ባድማ ይሆ​ናሉ፤ የሚ​ኖ​ር​ባ​ቸ​ውም የለም። 10የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ በቸ​ልታ የሚ​ያ​ደ​ርግ ርጉም ይሁን፤ ሰይ​ፉ​ንም ከደም የሚ​ከ​ለ​ክል ርጉም ይሁን።
11“ሞአብ ከል​ጅ​ነቷ ጀምራ ዐረ​ፈች፤ በክ​ብ​ር​ዋም ቅም​ጥል ነበ​ረች፤ ወይ​ን​ዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አል​ተ​ገ​ላ​በ​ጠም፤ ወደ ምር​ኮም አል​ሄ​ደ​ችም፤ ስለ​ዚህ ቃናው በእ​ር​ስዋ ውስጥ ቀር​ቶ​አል፤ መዓ​ዛ​ዋም አል​ተ​ለ​ወ​ጠም። 12ስለ​ዚህ እነሆ ጠማ​ሞ​ችን የም​ል​ክ​በት ዘመን ይመ​ጣል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሙ​በ​ታል፤ ጋኖ​ቹ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣሉ፤ ፊቀ​ኖ​ቹ​ንም ይሰ​ብ​ራሉ። 13የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ይታ​መ​ን​ባት ከነ​በ​ረው ከቤ​ቴል እን​ዳ​ፈረ፥ እን​ዲሁ ሞአብ ከካ​ሞሽ ታፍ​ራ​ለች። 14እና​ንተ፦ እኛ ኀያ​ላን በሰ​ል​ፍም ጽኑ​ዓን ነን እን​ዴት ትላ​ላ​ችሁ? 15ሞዓብ ፈር​ሳ​ለች፤ ከተ​ሞ​ቹ​ዋም ጠፍ​ተ​ዋል፤ የተ​መ​ረ​ጡ​ትም ጐል​ማ​ሶ​ችዋ ወደ መታ​ረድ ወር​ደ​ዋል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 16የሞ​አብ ጥፋት ሊመጣ ቀር​ቦ​አል፤ መከ​ራ​ውም እጅግ ይፈ​ጥ​ናል። 17በዙ​ሪ​ያው ያላ​ችሁ ሁሉ ስሙ​ንም የም​ታ​ውቁ ሁሉ፦ ታላቁ በትር፥ ጠን​ካ​ራ​ውም ሽመል፥ እን​ዴት ተሰ​በረ! ብላ​ችሁ አል​ቅ​ሱ​ለት። 18በዲ​ቦን የም​ት​ኖሪ ሆይ! ሞአ​ብን የሚ​ያ​ጠፋ ወጥ​ቶ​ብ​ሻ​ልና፥ አም​ባ​ሽ​ንም ሰብ​ሮ​አ​ልና ከክ​ብ​ርሽ ውረጂ፤ በጭ​ቃም ላይ ተቀ​መጪ። 19በአ​ሮ​ዔር የም​ት​ኖሪ ሆይ! በመ​ን​ገድ አጠ​ገብ ቆመሽ ተመ​ል​ከቺ፤ የሸ​ሸ​ው​ንና ያመ​ለ​ጠ​ውን፦ ምን ሆኖ​አል? ብለሽ ጠይ​ቂው።
20“ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ። 21ፍርድ ይመ​ጣል፤ በሜ​ሶር ምድር፥ በኬ​ሎን፥ በያ​ሳና፥ በሜ​ፍ​ዓት#ግእዝ “ራባስ” ይላል። ላይ፤ 22በዲ​ቦን፥ በና​ባው፥ በቤ​ት​ዲ​ብ​ላ​ታ​ይም ላይ፥ 23በቂ​ር​ያ​ታ​ይም፥ በቤ​ት​ጋ​ሙል፥ በቤ​ት​ም​ዖን ላይ፥ 24በቂ​ር​ዮት፥ በቦ​ሶራ፥ በሞ​አ​ብም ምድር ከተ​ሞች ሁሉ ቅር​ብና ሩቅ በሆኑ ላይ ፍርድ መጥ​ቶ​አል። 25የሞ​አብ ቀንድ ተሰ​በረ፤ እጁም ተቀ​ጠ​ቀጠ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
ሞአብ እንደ ተዋ​ረደ
26“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰር​ቶ​አ​ልና፥ አስ​ክ​ሩት፤ ሞአ​ብም በት​ፋቱ ላይ ይን​ከ​ባ​ለ​ላል፤ በእ​ጁም ያጨ​በ​ጭ​ባል፤ ደግሞ መሳ​ቂያ ይሆ​ናል። 27እስ​ራ​ኤል ለአ​ንተ መሳ​ቂያ አል​ሆ​ነ​ምን? ወይስ በሌ​ቦች መካ​ከል ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልን? ስለ እርሱ በተ​ና​ገ​ርህ ጊዜ ራስ​ህን ትነ​ቀ​ን​ቃ​ለህ። 28በሞ​አብ የሚ​ኖሩ ከተ​ሞ​ችን ትተው በዓ​ለት ውስጥ ተቀ​መጡ፤ በገ​ደል አፋ​ፍም ቤቷን እን​ደ​ም​ት​ሠራ እንደ ርግብ ሆኑ። 29የሞ​አ​ብን ስድብ፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንም ብዙ ውር​ደ​ቱን፥ ልቡ​ና​ው​ንም ያስ​ታ​በ​የ​በ​ትን ትዕ​ቢ​ቱን ሰም​ተ​ናል። 30እኔ ሥራ​ውን አው​ቃ​ለሁ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ እንደ ኀይ​ሉም መጠን እን​ዲሁ ያደ​ረገ አይ​ደ​ለም። 31ሰለ​ዚህ ለሞ​አብ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ለሞ​አ​ብም ሁሉ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች አለ​ቅ​ሳ​ለሁ። 32አንቺ የሴ​ባማ ወይን ሆይ! የኢ​ያ​ዜ​ርን ልቅሶ ለአ​ንቺ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ቅር​ን​ጫ​ፎ​ችሽ ባሕ​ርን ተሻ​ግ​ረ​ዋል፤ ወደ ኢያ​ዜ​ርም ባሕር#ግሪክ ሰባ. ሊ. “ከተማ” ይላል። ደር​ሰ​ዋል፤ ሳይ​በ​ስል#“ሳይ​በ​ስል” የሚ​ለው በዕብ. እና በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በሰ​ብ​ል​ሽና በወ​ይ​ንሽ ላይ ጥፋት መጥ​ቶ​አል። 33ሐሤ​ትና ደስታ ከፍ​ሬ​ያ​ማው እር​ሻና ከሞ​አብ ምድር ጠፍ​ተ​ዋል፤ ወይን ከመ​ጥ​መ​ቂ​ያው ጠፍ​ቶ​አል፤ በነ​ግህ የሚ​ጠ​ም​ቁት የለም፤ በሠ​ር​ክም የሚ​ያ​ደ​ር​ጉት የእ​ል​ልታ ድምፅ የለም። 34ከሐ​ሴ​ቦን ጩኸት እስከ ኤሊ​ያ​ሊና እስከ ኢያሳ ድረስ ድም​ፃ​ቸ​ውን ሰጥ​ተ​ዋል፤ ከሴ​ጎር እስከ ሖሮ​ና​ይ​ምና እስከ ዔግ​ላት ሺሊ​ሺያ ድረስ ይደ​ር​ሳል፤#ግእ​ዝና ግሪክ ሰባ. ሊ. “የሦ​ስት ዓመት ጊደር” ይላሉ። የኔ​ም​ሬም ውኃ ደር​ቋ​ልና። 35ሞአ​ብ​ንና በኮ​ረ​ብ​ታው መስ​ገጃ ላይ የሚ​ሠ​ዋ​ውን፥ ለአ​ማ​ል​ክ​ቱም የሚ​ያ​ጥ​ነ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።
36“ያተ​ረ​ፈው ትርፉ ጠፍ​ቶ​በ​ታ​ልና#“ያተ​ረ​ፈው ትርፉ ጠፍ​ቶ​በ​ታ​ልና” የሚ​ለው በግ​እዝ የለም። ስለ​ዚህ ልቤ ለሞ​አብ እንደ እን​ቢ​ልታ ይጮ​ኻል፤ ልቤም ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች እንደ እን​ቢ​ልታ ይጮ​ኻል፤ 37በሰው ሁሉ ራስ ላይ ቡሃ​ነት አለ፤ ጽሕ​ማ​ቸ​ውን ሁሉ ይላ​ጫሉ፤ እጆች ሁሉ ይን​ቀ​ጠ​ቀ​ጣሉ፤ ሁሉም በወ​ገ​ባ​ቸው ማቅን ይታ​ጠ​ቃሉ። 38ሞአ​ብ​ንም ለም​ንም እን​ደ​ማ​ይ​ጠ​ቅም ዕቃ ሰብ​ሬ​አ​ለ​ሁና በሞ​አብ ሰገ​ነት ሁሉ ላይ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ላይ ልቅሶ አለ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 39እን​ዴት ተለ​ወ​ጠች! ከእ​ፍ​ረ​ትም የተ​ነሣ ሞአብ ጀር​ባ​ዋን እን​ዴት መለ​ሰች! ሞአ​ብም በዙ​ሪ​ያዋ ላሉት ሁሉ መሳ​ቂ​ያና መሳ​ለ​ቂያ ትሆ​ና​ለች።
40እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፥ “እነሆ እንደ ንስር ይበ​ር​ራል፤ ክን​ፉ​ንም በሞ​አብ ላይ ይዘ​ረ​ጋል።#“እንደ ንስር ይበ​ር​ራል ፤ ክን​ፉ​ንም በሞ​አብ ላይ ይዘ​ረ​ጋል” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 41ሐቄ​ር​ዮት ተያ​ዘች፤ አን​ባ​ዎ​ች​ዋም ተወ​ስ​ደ​ዋል፤ በዚ​ያም ቀን የሞ​አብ ኀያ​ላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆ​ናል። 42ሞአ​ብም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ላይ ኰር​ታ​ለ​ችና ሕዝብ ከመ​ሆን ትጠ​ፋ​ለች። 43በሞ​አብ የም​ት​ኖር ሆይ! ፍር​ሀ​ትና ጕድ​ጓድ፥ ወጥ​መ​ድም በአ​ንተ ላይ አሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ 44እር​ስ​ዋን በም​ጐ​በ​ኝ​በት ዓመት በሞ​አብ ላይ ይህን አመ​ጣ​ለሁ፤ በፍ​ር​ሀት የሸሸ በጕ​ድ​ጓድ ውስጥ ይወ​ድ​ቃል፤ ከጕ​ድ​ጓ​ድም የወጣ በወ​ጥ​መድ ይያ​ዛል፤ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 45ከሰ​ልፍ የሸሹ ከሐ​ሴ​ቦን ጥላ በታች ቆመ​ዋል፤ እሳት ከሐ​ሴ​ቦን፥ ነበ​ል​ባ​ልም ከሴ​ዎን ወጥ​ቶ​አል፤ የሞ​አ​ብ​ንም ማዕ​ዘን፥ የሚ​ጮኹ ልጆ​ች​ንም ራስ በል​ቶ​አል። 46ሞአብ ሆይ! ወዮ​ልሽ! የካ​ሞሸ ወገን ጠፍ​ቶ​አል፤ ወን​ዶች ልጆ​ችሽ ተማ​ር​ከው ተወ​ስ​ደ​ዋ​ልና፥ ሴቶች ልጆ​ች​ሽም ወደ ምርኮ ሄደ​ዋ​ልና። 47ነገር ግን በኋ​ለ​ኛው ዘመን የሞ​አ​ብን ምርኮ እመ​ል​ሳ​ለሁ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። የሞ​ዓብ ፍርድ እስ​ከ​ዚህ ድረስ ነው።#ከምዕ. 48 ከቍ. 45 እስከ 47 ያለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ