ትንቢተ ኤርምያስ 47
47
በፍልስጥኤም ላይ የተነገረ ትንቢት
1ፈርዖንም ጋዛን ሳይመታ ስለ ፍልስጥኤማውያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤርምያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው።#ምዕ. 47 ቍ. 1 በግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ ነው። 2እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰሜን ይነሣል፥ የሚያጥለቀልቅም ፈሳሽ ይሆናል፤ በሀገሪቱና በመላዋ ሁሉ፥ በከተማዪቱና በሚኖሩባትም ላይ ይጐርፋል፤ ሰዎቹም ይጮኻሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ያለቅሳሉ። 3ከኀይለኞች ፈረሶች ከኮቴያቸው መጠብጠብ ድምፅ፥ ከሰረገሎቹም መሽከርከር፥ ከመንኰራኵሮቹም መትመም የተነሣ አባቶች በእጃቸው ድካም ምክንያት ወደ ልጆቻቸው አይመለሱም። 4ይህም የሚሆነው ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮስንና ሲዶናን የቀሩትንም ረዳቶቻቸውን ታጠፋ ዘንድ ስለምትመጣው ቀን ነው፤ እግዚአብሔር ፍልስጥኤማውያንንና በከፍቶር ደሴት የቀሩትን ያጠፋልና። 5ቡሀነት በጋዛ ላይ መጥቶአል፤ አስቀሎና ጠፋች፤ የዔናቅ ቅሬታዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትነጫላችሁ?#“እስከ መቼ ድረስ ገላችሁን ትነጫላችሁ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 6አንተ የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ! ዝም የማትለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገባህ ግባ፤ ጸጥ ብለህም ዕረፍ። 7እግዚአብሔር በአስቀሎናና በባሕር ዳር በቀሩትም ቦታዎች#“በቀሩትም ቦታዎች” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። ላይ ትእዛዝ ሰጥቶአልና፥ በዚያም አዘጋጅቶታልና#“አዘጋጅቶታልና” የሚለው ብዕብ. ብቻ። እንዴት ዝም ትላለህ? #“በዚያ ትነሣለህ” የሚለው በዕብ. የለም።በዚያ ትነሣለህ። #ምዕ. 47 በግሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 29 ነው።
Currently Selected:
ትንቢተ ኤርምያስ 47: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ