ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 47

47
በፍ​ል​ስ​ጥ​ኤም ላይ የተ​ነ​ገረ ትን​ቢት
1ፈር​ዖ​ንም ጋዛን ሳይ​መታ ስለ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።#ምዕ. 47 ቍ. 1 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ ነው። 2እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ ውኃ ከሰ​ሜን ይነ​ሣል፥ የሚ​ያ​ጥ​ለ​ቀ​ል​ቅም ፈሳሽ ይሆ​ናል፤ በሀ​ገ​ሪ​ቱና በመ​ላዋ ሁሉ፥ በከ​ተ​ማ​ዪ​ቱና በሚ​ኖ​ሩ​ባ​ትም ላይ ይጐ​ር​ፋል፤ ሰዎ​ቹም ይጮ​ኻሉ፤ በም​ድ​ርም የሚ​ኖሩ ሁሉ ያለ​ቅ​ሳሉ። 3ከኀ​ይ​ለ​ኞች ፈረ​ሶች ከኮ​ቴ​ያ​ቸው መጠ​ብ​ጠብ ድምፅ፥ ከሰ​ረ​ገ​ሎ​ቹም መሽ​ከ​ር​ከር፥ ከመ​ን​ኰ​ራ​ኵ​ሮ​ቹም መት​መም የተ​ነሣ አባ​ቶች በእ​ጃ​ቸው ድካም ምክ​ን​ያት ወደ ልጆ​ቻ​ቸው አይ​መ​ለ​ሱም። 4ይህም የሚ​ሆ​ነው ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንን ሁሉ ታጠፋ ዘንድ፥ ጢሮ​ስ​ንና ሲዶ​ናን የቀ​ሩ​ት​ንም ረዳ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ታጠፋ ዘንድ ስለ​ም​ት​መ​ጣው ቀን ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ን​ንና በከ​ፍ​ቶር ደሴት የቀ​ሩ​ትን ያጠ​ፋ​ልና። 5ቡሀ​ነት በጋዛ ላይ መጥ​ቶ​አል፤ አስ​ቀ​ሎና ጠፋች፤ የዔ​ናቅ ቅሬ​ታ​ዎች ሆይ! እስከ መቼ ድረስ ገላ​ች​ሁን ትነ​ጫ​ላ​ችሁ?#“እስከ መቼ ድረስ ገላ​ች​ሁን ትነ​ጫ​ላ​ችሁ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። 6አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ ሆይ! ዝም የማ​ት​ለው እስከ መቼ ነው? ወደ ሰገ​ባህ ግባ፤ ጸጥ ብለ​ህም ዕረፍ። 7እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በአ​ስ​ቀ​ሎ​ናና በባ​ሕር ዳር በቀ​ሩ​ትም ቦታ​ዎች#“በቀ​ሩ​ትም ቦታ​ዎች” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ብቻ። ላይ ትእ​ዛዝ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ በዚ​ያም አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ታ​ልና#“አዘ​ጋ​ጅ​ቶ​ታ​ልና” የሚ​ለው ብዕብ. ብቻ። እን​ዴት ዝም ትላ​ለህ? #“በዚያ ትነ​ሣ​ለህ” የሚ​ለው በዕብ. የለም።በዚያ ትነ​ሣ​ለህ። #ምዕ. 47 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 29 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ