ትን​ቢተ ኤር​ም​ያስ 46

46
ግብፅ በከ​ር​ከ​ሚሽ ላይ ድል እንደ ሆነች
1በአ​ሕ​ዛብ ላይ ወደ ነቢዩ ወደ ኤር​ም​ያስ የመ​ጣው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ይህ ነው።#ግሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ ነው። 2በግ​ብፅ ላይ፤ በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ በከ​ር​ኬ​ማስ በነ​በ​ረው፥ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር በመ​ታው በግ​ብፅ ንጉሥ በፈ​ር​ዖን ኒካዑ ሠራ​ዊት፥
3“ጋሻና ጦር ያዙ፤ ወደ ሰል​ፍም ቅረቡ። 4ፈረ​ሰ​ኞች ሆይ፥ ፈረ​ሶ​ችን ጫኑና ውጡ፤ ራስ ቍር​ንም ደፍ​ታ​ችሁ ቁሙ፤ ጦር​ንም ሰን​ግሉ፤ ጥሩ​ር​ንም ልበሱ። 5ፈር​ተው ወደ ኋላ ሲመ​ለሱ፥ ኀያ​ላ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም ሲደ​ክሙ፥ ወደ ኋላ​ቸ​ውም ሳይ​መ​ለ​ከቱ ፈጥ​ነው ሲሸሹ ለምን አየሁ? በዙ​ሪ​ያ​ቸ​ውም ይከ​ቡ​አ​ቸ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 6ፈጣ​ኑም አያ​መ​ል​ጥም፤ ኀያ​ሉም አይ​ድ​ንም፤ በሰ​ሜን በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ በኩል ደክ​መው ወደቁ።
7ይህ እንደ ወንዝ የሚ​ነሣ ውኃ​ውም እንደ ወንዝ የሚ​ና​ወጥ ማን ነው? 8ግብፅ እንደ ወንዝ ይነ​ሣል፤ ከባ​ሕ​ሩም እን​ደ​ሚ​ታ​ወክ ማዕ​በል ይሆ​ናል፤ እር​ሱም እን​ዲህ ብሏል፥ “እነ​ሣ​ለሁ፤ ምድ​ር​ንም ሁሉ እከ​ድ​ና​ለሁ፤ ከተ​ሞ​ች​ንና የሚ​ኖ​ሩ​ባ​ቸ​ውን አጠ​ፋ​ለሁ። 9በፈ​ረ​ሶች ተቀ​መጡ፤ ሰረ​ገ​ሎ​ች​ንም አዘ​ጋ​ጁና ውጡ፤ ጋሻም የሚ​ያ​ነ​ግቡ የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያና የሊ​ብያ#ግእ​ዝና ዕብ. “ፉጥ” ይላል። ኀያ​ላን፥ ቀስ​ት​ንም ይዘው የሚ​ስቡ የሉድ ኀያ​ላን ይውጡ። 10ያ ቀን ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀ​ል​በት የአ​ም​ላ​ካ​ችን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የበ​ቀል ቀን ነው፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰይፍ በልቶ ይጠ​ግ​ባል፤ በደ​ማ​ቸ​ውም ይሰ​ክ​ራል፤ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት በሰ​ሜን ምድር በኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ አጠ​ገብ ነውና። 11ድን​ግ​ሊቱ የግ​ብፅ ልጅ ሆይ! ወደ ገለ​ዓድ ውጪ፤ የሚ​ቀባ መድ​ኀ​ኒ​ት​ንም ውሰጂ፤ ለም​ንም የማ​ይ​ጠ​ቅ​ም​ሽን መድ​ኀ​ኒት በከ​ንቱ አብ​ዝ​ተ​ሻል። 12ጦረ​ኞች በጦ​ረ​ኞች ላይ ተሰ​ና​ክ​ለው ሁለቱ በአ​ን​ድ​ነት ወድ​ቀ​ዋ​ልና አሕ​ዛብ ቃል​ሽን ሰም​ተ​ዋል፤ ልቅ​ሶ​ሽም ምድ​ርን ሞል​ቶ​አ​ታል።”
ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ ግብፅ እንደ መጣ
13የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እን​ደ​ሚ​መ​ጣና የግ​ብ​ፅን ምድር እን​ደ​ሚ​መታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለነ​ቢዩ ለኤ​ር​ም​ያስ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።
14“በግ​ብፅ ተና​ገሩ፤#“በግ​ብፅ ተና​ገሩ” የሚ​ለው በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም። በሚ​ግ​ዶ​ልም አውሩ፤ በሜ​ም​ፎ​ስና በጣ​ፍ​ናስ አሰሙ፤ ሰይፍ በዙ​ሪ​ያህ ያለ​ውን በል​ቶ​አ​ልና፦ ተነሥ ተዘ​ጋ​ጅም በሉ። 15ኀይ​ለ​ኞ​ችህ ስለ ምን ታጡ? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስላ​ደ​ከ​ማ​ቸው የሉም።#ግሪክ ሰባ. ሊ. “አፒስ ለምን ሸሸ​ፍክ? ምርጥ በሬ​ውም አል​ቆ​መም ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አድ​ክ​ሞ​አ​ቸ​ዋ​ልና” ይላል። 16ብዛ​ታ​ቸ​ውም ደከመ፤ ወደ​ቀም፤ አን​ዱም አንዱ ለጓ​ደ​ኛው፦ ተነሥ፤ ከአ​ረ​ማ​ው​ያን ሰይፍ ፊት ወደ ወገ​ና​ችን ወደ ተወ​ለ​ድ​ን​ባት ምድር እን​መ​ለስ አለው። 17በዚ​ያም የግ​ብፅ ንጉሥ የፈ​ር​ዖ​ንን ስም ጊዜ​ውን የሚ​ያ​ሳ​ልፍ ብለው ጠሩት። 18እኔ ሕያው ነኝና በተ​ራ​ሮች መካ​ከል እን​ዳለ እንደ አጤ​ቤ​ር​ዮን፥#ዕብ. “ታቦር” ይላል። በባ​ሕ​ርም አጠ​ገብ እን​ዳለ እንደ ቀር​ሜ​ሎስ፥ እን​ዲሁ በእ​ው​ነት ይመ​ጣል፥ ይላል ስሙ የሠ​ራ​ዊት ጌታ የሆነ ንጉሥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። 19አንቺ በግ​ብፅ የም​ት​ቀ​መጪ ልጅ ሆይ! ሜም​ፎስ ባድማ ትሆ​ና​ለ​ችና፥ የሚ​ቀ​መ​ጥ​ባ​ትም አይ​ገ​ኝ​ምና ለፍ​ል​ሰት የሚ​ሆን ዕቃ አዘ​ጋጂ።
20“ግብፅ የተ​ዋ​በች ጊደር ናት፤ ጥፋት ግን ከሰ​ሜን#ግእዝ “ከደ​ቡብ” ይላል። በኩል ይመ​ጣ​ባ​ታል። 21በእ​ር​ስ​ዋም ያሉ የተ​ቀ​ጠሩ ሠራ​ተ​ኞች በእ​ር​ስዋ ተቀ​ል​በው እንደ ሰቡ ወይ​ፈ​ኖች ናቸው፤ የጥ​ፋ​ታ​ቸው ቀንና የቅ​ጣ​ታ​ቸው ጊዜ መጥ​ቶ​ባ​ቸ​ዋ​ልና ተመ​ለሱ፤ በአ​ን​ድ​ነ​ትም ሸሹ፤ አል​ቆ​ሙ​ምም። 22ሠራ​ዊ​ትም በኀ​ይል ይዘ​ም​ቱ​ባ​ታ​ልና፥ እንደ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችም በም​ሳር ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ድም​ፅዋ እን​ደ​ም​ት​ሸሽ እባብ ይተ​ማል። 23ሊቈ​ጠሩ የማ​ይ​ችሉ የዱ​ር​ዋን ዛፎች ይቈ​ር​ጣሉ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከአ​ን​በጣ ይልቅ በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ቍጥ​ርም የላ​ቸ​ው​ምና። 24የግ​ብፅ ልጅ ታፍ​ራ​ለች፤ በሰ​ሜን ሕዝብ እጅም አልፋ ትሰ​ጣ​ለች።” 25የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ የኖእ አሞ​ንን፥ ፈር​ዖ​ን​ንም፥ ግብ​ጽ​ንም፥ አማ​ል​ክ​ቶ​ች​ዋ​ንና ነገ​ሥ​ታ​ቶ​ች​ዋ​ንም፥ ፈር​ዖ​ን​ንና በእ​ር​ሱም የሚ​ታ​መ​ኑ​ትን እቀ​ጣ​ለሁ።#ምዕ. 46 ቍ. 25 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ልዩ ነው። 26ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ፈ​ልጉ ሰዎች እጅ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”#ምዕ. 46 ቍ. 26 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. የለም።
እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕዝ​ቡን እን​ደ​ሚ​ታ​ደግ
27“ነገር ግን አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! አት​ፍራ፥ አን​ተም እስ​ራ​ኤል ሆይ! አት​ደ​ን​ግጥ፤ እነሆ አን​ተን ከሩቅ፥ ዘር​ህ​ንም ከተ​ማ​ረ​ኩ​ባት ምድር አድ​ና​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብም ተመ​ልሶ ያር​ፋል፤ ተዘ​ል​ሎም ይተ​ኛል፤ ማንም አያ​ስ​ፈ​ራ​ውም። 28አንተ ባሪ​ያዬ ያዕ​ቆብ ሆይ! እኔ ከአ​ንተ ጋር ነኝና አት​ፍራ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ አን​ተ​ንም ያሳ​ደ​ድ​ሁ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛ​ብን ሁሉ ፈጽሜ አጠ​ፋ​ለ​ሁና፥ አን​ተን ግን ፈጽሜ አላ​ጠ​ፋ​ህም፤ በመ​ጠን እቀ​ጣ​ሃ​ለሁ፥ ያለ ቅጣ​ትም አል​ተ​ው​ህም።”#ምዕ. 46 በግ​ሪክ ሰባ. ሊ. ምዕ. 26 ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ