መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 5:19-31

መጽ​ሐፈ መሳ​ፍ​ንት 5:19-31 አማ2000

ነገ​ሥ​ታት መጡ፤ ተዋ​ጉም፤ በዚያ ጊዜ በመ​ጌዶ ውኆች አጠ​ገብ በቶ​ናሕ የከ​ነ​ዓን ነገ​ሥ​ታት ተዋጉ፤ በቅ​ሚ​ያም ብርን አል​ወ​ሰ​ዱም። ከዋ​ክ​ብት በሰ​ማይ ተዋጉ፤ በሰ​ል​ፋ​ቸ​ውም ከሲ​ሣራ ጋር ተዋጉ። ከዱሮ ጀምሮ የታ​ወቀ ያ የቂ​ሶን ወንዝ፥ የቂ​ሶን ወንዝ ጠርጎ ወሰ​ዳ​ቸው። ነፍሴ ሆይ፥ በርቺ። ያን ጊዜ ከኀ​ያ​ላን ግል​ቢያ ብር​ታት የተ​ነሣ፥ የፈ​ረ​ሶች ጥፍ​ሮች ተቀ​ጠ​ቀጡ። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መል​አክ አለ፥ “ሜሮ​ዝን ርገሙ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በኀ​ያ​ላን መካ​ከል ወደ እርሱ ርዳታ አል​መ​ጡ​ምና፥ በቤ​ቶ​ችዋ ያሉ​ትን ሰዎች ፈጽ​ማ​ችሁ ርገሙ።” የቄ​ና​ዊው የሔ​ቤር ሚስት ኢያ​ዔል፥ ከሴ​ቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን፤ በድ​ን​ኳን ውስጥ ከሚ​ኖሩ ሴቶች ይልቅ የተ​ባ​ረ​ከች ትሁን። ውኃ ለመነ፤ ወተ​ትም ሰጠ​ችው፤ በተ​ከ​በረ ዳካ እርጎ አቀ​ረ​በ​ች​ለት። ግራ እጅ​ዋን ወደ ካስማ፤ ቀኝ እጅ​ዋ​ንም ወደ ሠራ​ተኛ መዶሻ አደ​ረ​ገች፤ በመ​ዶ​ሻ​ውም ሲሣ​ራን መታ​ችው፤ ራሱ​ንም ቸነ​ከ​ረች፤ ጆሮ ግን​ዱ​ንም በሳች፤ ጐዳ​ች​ውም። በእ​ግ​ሮ​ችዋ አጠ​ገብ ተደፋ፤ ወደቀ፤ ተኛ፤ በእ​ግ​ሮ​ችዋ አጠ​ገብ ተፈ​ራ​ገጠ፤ በተ​ፈ​ራ​ገ​ጠ​በ​ትም በዚያ ተጐ​ሳ​ቍሎ ሞተ። የሲ​ሣራ እናት በመ​ስ​ኮት ሆና ተመ​ለ​ከ​ተች፤ በሰ​ቅ​ሰ​ቅም ዘልቃ፦ ከሲ​ሣራ የተ​መ​ለሰ እን​ዳለ አየች፤ ስለ​ምን ለመ​ም​ጣት ሰረ​ገ​ላው ዘገየ? ስለ​ም​ንስ የሰ​ረ​ገ​ላው መን​ኰ​ራ​ኵር ቈየ? ብላ ጮኸች። ብል​ሃ​ተ​ኞች ሴቶ​ችዋ መለ​ሱ​ላት፤ እር​ስዋ ደግሞ ለራ​ስዋ እን​ዲህ ብላ መለ​ሰች፦ ምር​ኮ​ውን ሲካ​ፈል፥ በኀ​ያ​ላ​ኑም ቸብ​ቸቦ ላይ ወዳ​ጆ​ችን ሲወ​ዳጅ ያገ​ኙት አይ​ደ​ለ​ምን? የሲ​ሣራ ምርኮ በየ​ኅ​ብሩ ነበረ፤ የኅ​ብ​ሩም ቀለም የተ​ለ​ያየ ነበረ፤ የማ​ረ​ከ​ውም ወርቀ ዘቦ ግምጃ በአ​ን​ገቱ ላይ ነበረ። አቤቱ ጠላ​ቶ​ችህ ሁሉ እን​ዲሁ ይጥፉ፤ ወዳ​ጆ​ችህ ግን ፀሐይ በኀ​ይሉ በወጣ ጊዜ እን​ደ​ሚ​ሆን፤ እን​ዲሁ ይሁኑ። ምድ​ሪ​ቱም አርባ ዓመት ያህል ዐረ​ፈች።