ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 7:13-16

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 7:13-16 አማ2000

እር​ሱም አለ፥ “እና​ንተ የዳ​ዊት ቤት ሆይ፥ ስሙ፤ በውኑ ሰውን ማድ​ከ​ማ​ችሁ ቀላል ነውን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታደ​ክ​ማ​ላ​ችሁ፤ ስለ​ዚህ ጌታ ራሱ ምል​ክት ይሰ​ጣ​ች​ኋል፤ እነሆ፥ ድን​ግል ትፀ​ን​ሳ​ለች፤ ወንድ ልጅ​ንም ትወ​ል​ዳ​ለች፤ ስሙ​ንም አማ​ኑ​ኤል ብላ ትጠ​ራ​ዋ​ለች። ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት መል​ካ​ሙ​ንም ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ ቅቤና ማር ይበ​ላል። ሕፃኑ ክፉን ለመ​ጥ​ላት፥ መል​ካ​ሙን ለመ​ም​ረጥ ሳያ​ውቅ፥ የፈ​ራ​ሃ​ቸው የሁ​ለቱ ነገ​ሥ​ታት ሀገር ባድማ ትሆ​ና​ለች።