ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 28:9-13

ትን​ቢተ ኢሳ​ይ​ያስ 28:9-13 አማ2000

ክፉን ለማን ተና​ገ​ርን? ወሬን ለማን አወ​ራን? ወተ​ትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? ሕማ​ምን በሕ​ማም ላይ፥ ተስ​ፋ​ንም በተ​ስፋ ላይ ተቀ​በሉ፤ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው። በባ​ዕድ አፍ በል​ዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይና​ገ​ራል፤ እር​ሱም፥ “ይህ​ችም ለደ​ከመ ዕረ​ፍት ናት፤ ይህ​ችም መቅ​ሠ​ፍት ናት፤” አላ​ቸው፤ እነ​ርሱ ግን መስ​ማ​ትን እንቢ አሉ። ስለ​ዚህ ሄደው ወደ ኋላ እን​ዲ​ወ​ድቁ፥ እን​ዲ​ሰ​በ​ሩም፥ ተጠ​ም​ደ​ውም እን​ዲ​ቸ​ገሩ፥ የግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃሉ በሕ​ማም ላይ ሕማም፥ በተ​ስፋ ላይ ተስፋ፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆ​ን​ላ​ቸ​ዋል።