ትን​ቢተ ሆሴዕ 12:7-14

ትን​ቢተ ሆሴዕ 12:7-14 አማ2000

ስለ​ዚህ ወደ አም​ላ​ክህ ተመ​ለስ፤ ምሕ​ረ​ት​ንና ፍር​ድን ጠብቅ፤ ዘወ​ት​ርም ወደ አም​ላ​ክህ ቅረብ። በከ​ነ​ዓን እጅ የዐ​መፅ ሚዛን አለ፤ ቅሚ​ያ​ንም ይወ​ድ​ዳል። ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ባለ​ጸጋ ሆኜ​አ​ለሁ፤ ሀብ​ት​ንም አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፤ በድ​ካ​ሜም ሁሉ ኀጢ​አት የሚ​ሆን በደል አይ​ገ​ኝ​ብ​ኝም” አለ። እኔም ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀንም እንደ ገና በድ​ን​ኳን አስ​ቀ​ም​ጥ​ሃ​ለሁ። ለነ​ቢ​ያ​ትም ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ፤ ራእ​ይ​ንም አብ​ዝ​ቻ​ለሁ፤ በነ​ቢ​ያ​ትም እጅ ተመ​ስ​ያ​ለሁ። በገ​ለ​ዓድ ባይ​ሆ​ንም እንኳ በጌ​ል​ጌላ መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን የሚ​ሠዉ አለ​ቆች ስተ​ዋል፤ መሠ​ዊ​ያ​ዎ​ቻ​ቸ​ውም በእ​ርሻ ትልም ላይ እንደ አለ የድ​ን​ጋይ ክምር ነው። ያዕ​ቆብ ወደ ሶርያ ሀገር ሸሸ፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ስለ ሚስት አገ​ለ​ገለ፤ ስለ ሚስ​ትም ጠበቀ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በነ​ቢይ እስ​ራ​ኤ​ልን ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣው፤ በነ​ቢ​ይም ጠበ​ቀው።