ትን​ቢተ ሆሴዕ 10:11-13

ትን​ቢተ ሆሴዕ 10:11-13 አማ2000

ኤፍ​ሬ​ምም ቀን​በ​ርን እንደ ለመ​ደች ጊደር ነው፤ እኔ ግን በአ​ን​ገቱ ውበት እጫ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ በኤ​ፍ​ሬም ላይ እጠ​ም​ድ​በ​ታ​ለሁ፤ ይሁ​ዳ​ንም እለ​ጕ​መ​ዋ​ለሁ፤ ያዕ​ቆ​ብም ለራሱ መን​ግ​ሥ​ትን ያስ​ተ​ካ​ክ​ላል። ለእ​ና​ንተ ጽድ​ቅን ዝሩ፤ የሕ​ይ​ወት ፍሬን ሰብ​ስቡ፤ የጥ​በ​ብ​ንም ብር​ሃን ለራ​ሳ​ችሁ አብሩ፤ የጽ​ድ​ቃ​ችሁ መከር እስ​ኪ​ደ​ርስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት። ዐመ​ፅን ለምን ተከ​ላ​ችሁ? ኀጢ​አ​ት​ንስ ለምን አጨ​ዳ​ችሁ፤ የሐ​ሰ​ት​ንም ፍሬ በል​ታ​ች​ኋል፤ በሠ​ረ​ገ​ሎ​ች​ህና በሠ​ራ​ዊ​ትህ ብዛት ታም​ነ​ሃል።