ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 25:23-26

ኦሪት ዘፍ​ጥ​ረት 25:23-26 አማ2000

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አላት፥ “ሁለት ሕዝ​ቦች በማ​ኅ​ፀ​ንሽ አሉ፤ ሁለ​ቱም ሕዝብ ከሆ​ድሽ ይወ​ለ​ዳሉ፤ ሕዝ​ብም ከሕ​ዝብ ይበ​ረ​ታል፤ ታላ​ቁም ለታ​ናሹ ይገ​ዛል።” የም​ት​ወ​ል​ድ​በ​ትም ወራት ተፈ​ጸመ፤ በማ​ኅ​ፀ​ን​ዋም መንታ ነበሩ። የበ​ኵር ልጅ​ዋም ወጣ፤ እንደ ጽጌ​ረ​ዳም ቀይ ነበረ፤ ሁለ​ን​ተ​ና​ውም ጠጕ​ራም ነበር፤ ስሙ​ንም ዔሳው ብላ ጠራ​ችው። ከዚ​ያም በኋላ ወን​ድሙ ወጣ፤ በእ​ጁም የዔ​ሳ​ውን ተረ​ከዝ ይዞ ነበር፤ ስሙ​ንም ያዕ​ቆብ ብላ ጠራ​ችው። ርብቃ ዔሳ​ው​ንና ያዕ​ቆ​ብን በወ​ለ​ደ​ቻ​ቸው ጊዜ ይስ​ሐቅ ስድሳ ዓመት ሆኖት ነበር።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}