ኦሪት ዘፀ​አት 24:13-18

ኦሪት ዘፀ​አት 24:13-18 አማ2000

ሙሴም ከኢ​ያሱ ጋር ተነሣ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተራ​ራም ወጡ። ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ች​ንም፥ “ወደ እና​ንተ እስ​ክ​ን​መ​ለስ ድረስ በዚህ ቈዩን፤ ግር​ግር አት​በሉ፤ አሮ​ንና ሆርም እነሆ፥ ከእ​ና​ንተ ጋር ናቸው፤ ነገ​ረ​ተ​ኛም ቢኖር ወደ እነ​ርሱ ይሂድ” አላ​ቸው። ሙሴም ከኢ​ያሱ ጋር ወደ ተራራ ወጣ፤ ደመ​ና​ውም ተራ​ራ​ውን ሸፈ​ነው። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ክብር በሲና ተራራ ላይ ወረደ፤ ደመ​ና​ውም ስድ​ስት ቀን ሸፈ​ነው፤ በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከደ​መ​ናው ውስጥ ሙሴን ጠራው። በተ​ራ​ራ​ውም ራስ ላይ በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ክብር መታ​የት እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት ነበረ። ሙሴም ወደ ደመ​ናው ውስጥ ገባ፤ ወደ ተራ​ራ​ውም ወጣ፤ ሙሴም በተ​ራ​ራው ላይ አርባ ቀን፥ አርባ ሌሊ​ትም ቈየ።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}