መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 5:10-12

መጽ​ሐፈ መክ​ብብ 5:10-12 አማ2000

ብርን የሚ​ወ​ድድ ሰው ብርን አይ​ጠ​ግ​ብም፤ ብዙ እህ​ል​ንም የሚ​ወ​ድድ እን​ዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው። ሀብት ሲበዛ የሚ​በ​ሉት ይበ​ዛሉ፤ በዐ​ይ​ኑም ከማ​የት በቀር ለባ​ለ​ቤቱ ምን ይጠ​ቅ​መ​ዋል? ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአ​ገ​ል​ጋይ እን​ቅ​ልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብል​ጽ​ግ​ናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚ​ተ​ወው የለም።