መክብብ 5:10-12
መክብብ 5:10-12 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)
ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፤ ብዙ እህልንም የሚወድድ እንዲሁ ነው፤ ይህም ከንቱ ነው። ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፤ በዐይኑም ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? ብዙ ወይም ጥቂት ቢበላ የአገልጋይ እንቅልፉ ጣፋጭ ነው፤ ብልጽግናን ያበዛ ሰውን ግን ይተኛ ዘንድ የሚተወው የለም።
ያጋሩ
መክብብ 5 ያንብቡመክብብ 5:10-12 አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)
ገንዘብን የሚወድድ፣ ገንዘብ አይበቃውም፤ ብልጽግናም የሚወድድ፣ በትርፉ አይረካም፤ ይህም ከንቱ ነው። ሀብት በበዛ ቍጥር፣ ተጠቃሚውም ይበዛል፤ በዐይኑ ብቻ ከማየት በቀር ታዲያ፣ ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? ጥቂትም ይሁን ብዙ ቢበላ፣ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው፤ የሀብታም ሰው ብልጽግና ግን እንቅልፍ ይነሣዋል።
ያጋሩ
መክብብ 5 ያንብቡመክብብ 5:10-12 መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) (አማ54)
ብርን የሚወድድ ሰው ብርን አይጠግብም፥ ባለጠግነትንም የሚወድድ ትርፉን አይጠግብም፥ ይህም ደግሞ ከንቱ ነው። ሀብት ሲበዛ የሚበሉት ይበዛሉ፥ ሀብቱን በዓይኑ ብቻ ከማየት በቀር ለባለቤቱ ምን ይጠቅመዋል? እጅግ ወይም ጥቂት ቢበላ የሠራተኛ እንቅልፍ ጣፋጭ ነው የባለጠጋ ጥጋብ ግን እንቅልፍን ይከለክለዋል።
ያጋሩ
መክብብ 5 ያንብቡ