ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 1:13-23

ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 1:13-23 አማ2000

ከጨ​ለማ አገ​ዛዝ አዳ​ነን፤ ወደ ተወ​ደ​ደው ልጁ መን​ግ​ሥ​ትም መለ​ሰን። ድኅ​ነ​ትን ያገ​ኘ​ን​በት፥ ኀጢ​አ​ታ​ች​ንም የተ​ሠ​ረ​የ​በት ነው። ይኸ​ውም የማ​ይ​ታይ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​መ​ስ​ለው፥ ከፍ​ጥ​ረቱ ሁሉ በላይ የሆነ በኵር ነው። በእ​ርሱ ቃል​ነት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሁሉን ፈጥ​ሮ​አ​ልና በሰ​ማይ ያለ​ውን፥ በም​ድ​ርም ያለ​ውን፥ የሚ​ታ​የ​ው​ንና የማ​ይ​ታ​የ​ውን፥ መና​ብ​ር​ትም ቢሆኑ፥ አጋ​እ​ዝ​ትም ቢሆኑ፥ መኳ​ን​ን​ትም ቢሆኑ፥ ቀደ​ም​ትም ቢሆኑ፥ ሁሉን በእ​ርሱ ቃል​ነት ፈጥ​ሮ​አ​ቸ​ዋ​ልና፤ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ለእ​ርሱ ተፈ​ጠረ፤ እርሱ ከሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ነበረ፤ ሁሉም በእ​ርሱ ጸና። እርሱ የቤተ ክር​ስ​ቲ​ያን ራስ ነው፤ በኵር እርሱ ለሁሉ ራስ ይሆን ዘንድ ከሙ​ታን ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አ​ልና። ሁሉ በእ​ርሱ ፍጹም ሆኖ ይኖር ዘንድ፥ ወዶ​አ​ልና። ሁሉ​ንም በእ​ርሱ ይቅር ይለው ዘንድ በመ​ስ​ቀሉ ባፈ​ሰ​ሰው ደም በም​ድ​ርና በሰ​ማ​ያት ላሉ ሰላ​ምን አደ​ረገ። እና​ን​ተም ቀድሞ በአ​ሳ​ባ​ች​ሁና በክፉ ሥራ​ችሁ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ለ​ያ​ች​ሁና ጠላ​ቶች ነበ​ራ​ችሁ። አሁን ግን በፊቱ ለመ​ቆም የተ​መ​ረ​ጣ​ች​ሁና ንጹ​ሓን፥ ቅዱ​ሳ​ንም ያደ​ር​ጋ​ችሁ ዘንድ በሥ​ጋው ሰው​ነት በሞቱ ይቅር አላ​ችሁ። እን​ግ​ዲህ ከሰ​ማ​ች​ሁት ከሰ​ማይ በታች በመ​ላው ዓለም ከተ​ሰ​በ​ከው እኔ ጳው​ሎ​ስም አዋጅ ነጋ​ሪና መል​እ​ክ​ተኛ ሆኜ ከተ​ሾ​ም​ሁ​ለት፥ ከወ​ን​ጌል ትም​ህ​ርት ተስፋ የመ​ሠ​ረ​ታ​ችሁ አቅ​ዋም ሳይ​ና​ወጥ ጨክ​ና​ችሁ በሃ​ይ​ማ​ኖት ብት​ጸኑ፥

ከ ወደ ቈላ​ስ​ይስ ሰዎች 1:13-23ጋር የተዛመዱ ነፃ የንባብ እቅዶች እና ምንባቦች