የሐዋርያት ሥራ 21:35-40
የሐዋርያት ሥራ 21:35-40 አማ2000
ደረጃውንም በሚወጣበት ጊዜ ወታደሮች ተሸክመው አወጡት፤ ሰው ይጋፋ ነበርና። ብዙዎችም ይከተሉት ነበር፤ ሕዝቡም፥ “አስወግዱት” እያሉ ይጮሁ ነበር። ወደ ሰፈርም በደረሰ ጊዜ ጳውሎስ ሻለቃውን፥ “ላነጋግርህ ትፈቅድልኛለህን?” አለው፤ ሻለቃውም፥ “የጽርዕ ቋንቋ ታውቃለህን?” አለው። “ምናልባት ከዚህ በፊት ወንጀል የሠራህና ከነፍሰ ገዳዮች አራት ሺህ ሰዎችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወጣህ ያ ግብፃዊ አንተ አይደለህምን?” አለው። ጳውሎስም፥ “እኔስ አይሁዳዊ ሰው ነኝ፤ የተወለድሁባትም ሀገር ጠርሴስ የታወቀች የቂልቅያ ከተማ ናት፤ ለሕዝቡም እንድነግራቸው ትፈቅድልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” አለው። በፈቀደለትም ጊዜ ጳውሎስ በደረጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳውሎስ በዕብራይስጥ ቋንቋ ተናገረ፤ እንዲህም አለ።

