ሐዋርያት ሥራ 21:35-40

ሐዋርያት ሥራ 21:35-40 የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) (አማ2000)

ደረ​ጃ​ው​ንም በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ ወታ​ደ​ሮች ተሸ​ክ​መው አወ​ጡት፤ ሰው ይጋፋ ነበ​ርና። ብዙ​ዎ​ችም ይከ​ተ​ሉት ነበር፤ ሕዝ​ቡም፥ “አስ​ወ​ግ​ዱት” እያሉ ይጮሁ ነበር። ወደ ሰፈ​ርም በደ​ረሰ ጊዜ ጳው​ሎስ ሻለ​ቃ​ውን፥ “ላነ​ጋ​ግ​ርህ ትፈ​ቅ​ድ​ል​ኛ​ለ​ህን?” አለው፤ ሻለ​ቃ​ውም፥ “የጽ​ርዕ ቋንቋ ታው​ቃ​ለ​ህን?” አለው። “ምና​ል​ባት ከዚህ በፊት ወን​ጀል የሠ​ራ​ህና ከነ​ፍሰ ገዳ​ዮች አራት ሺህ ሰዎ​ችን ይዘህ ወደ ምድረ በዳ የወ​ጣህ ያ ግብ​ፃዊ አንተ አይ​ደ​ለ​ህ​ምን?” አለው። ጳው​ሎ​ስም፥ “እኔስ አይ​ሁ​ዳዊ ሰው ነኝ፤ የተ​ወ​ለ​ድ​ሁ​ባ​ትም ሀገር ጠር​ሴስ የታ​ወ​ቀች የቂ​ል​ቅያ ከተማ ናት፤ ለሕ​ዝ​ቡም እን​ድ​ነ​ግ​ራ​ቸው ትፈ​ቅ​ድ​ልኝ ዘንድ እለ​ም​ን​ሃ​ለሁ” አለው። በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።