ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 12:8-10

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 2 12:8-10 አማ2000

ስለ​ዚ​ህም ከእኔ ያር​ቀው ዘንድ ጌታ​ዬን ሦስት ጊዜ ማለ​ድ​ሁት። እር​ሱም፥ “ጸጋዬ ይበ​ቃ​ሀል፤ ኀይ​ልስ በደዌ ያል​ቃል” አለኝ፤ የክ​ር​ስ​ቶ​ስም ኀይል በእኔ ላይ ያድር ዘንድ በመ​ከ​ራዬ ልመካ ወደ​ድሁ። ስለ​ዚ​ህም ስለ ክር​ስ​ቶስ መከራ መቀ​በ​ልን፥ መሰ​ደ​ብን፥ መጨ​ነ​ቅን፥ መሰ​ደ​ድን፥ መቸ​ገ​ር​ንም ወደ​ድሁ፤ መከራ በተ​ቀ​በ​ልሁ ጊዜ ወዲ​ያ​ውኑ እበ​ረ​ታ​ለ​ሁና።