መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 26
26
የእግዚአብሔር ቤት በረኞች
1በረኞችም እንደዚህ ተመደቡ፤ ከቆሬያውያን ከአሳፍ ልጆች የቆሬ ልጅ ሜሱላም። 2ሜሱላምም ልጆች ነበሩት፤ በኵሩ ዘካርያስ፥ ሁለተኛው ይዲኤል፥ ሦስተኛው ዘባድያ፥ አራተኛው የትንኤል፤ 3አምስተኛው ኤላም፥ ስድስተኛው ይሆሐናን፥ ሰባተኛው ኤሊሆዔናይ። 4ዖቤድኤዶምም ልጆች ነበሩት፤ በኵሩ ሰማያ፥ ሁለተኛው ዮዛባት፥ ሦስተኛው ኢዮአስ፥ አራተኛው ሣካር፥ አምስተኛው ናትናኤል፤ 5ስድስተኛው ዓሚኤል፥ ሰባተኛው ይሳኮር፥ ስምንተኛው ፒላቲ ነበሩ፤ አምላኩ እግዚአብሔር ባርኮታልና። 6ለልጁ ለሰማያም ከበኵር ልጁ ከሮሲ ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም በአባታቸው ቤት የሠለጠኑ እጅግም ኀያላን ነበሩ። 7የሰማያ ልጆች ዖትኒ፥ ራፋኤል፥ ዖቤድ፥ ወንድሞቹም ኀያላን የነበሩ ኤልዛባድ፥ ኤሊሁ፥ ሰማክያ፥ ኢስባኮም። 8እነዚህ ሁሉ የዖቤድኤዶም ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም፥ ልጆቻቸውም፥ ወንድሞቻቸውም ለማገልገል ኀያላን የነበሩ የዖቤድኤዶም ልጆች ስድሳ ሁለት ነበሩ። 9ለሜሱላምም ኀያላን የነበሩ ዐሥራ ስምንት ልጆችና ወንድሞች ነበሩት። 10ከሜራሪም ልጆች ለነበረው ለሖሳ ፊተኛውን በር የሚጠብቁ ልጆች ነበሩት፤ አለቃውም ሰምሪ ነበረ፤#“አለቃውም ሰምሪ ነበረ” የሚለው በዕብ. ብቻ። በኵር አልነበረም፤ አባቱ ግን አለቃ አደረገው፤ 11ሁለተኛውም ኬልቅያስ፥ ሦስተኛውም ጥበልያ፥ አራተኛውም ዘካርያስ ነበረ፤ የሖሳ ልጆችና ወንድሞች ሁሉ ዐሥራ ሦስት ነበሩ።
12እንደ ወንድሞቻቸው ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግሉ ዘንድ የበረኞች አለቆች በየሰሞናቸው የሚጠብቁ እነዚህ ነበሩ። 13በበሩም ሁሉ ያገለግሉ ዘንድ በየአባቶቻቸው ቤቶች ታናሹና ታላቁ ተካክለው ዕጣ ተጣጣሉ። 14የምሥራቁም በር ዕጣ ለሰሌምያና ለዘካርያ ወደቀ። የዮአስም ልጆች ለምልክያ ዕጣ ጣሉ፤ ዕጣውም በሰሜን በኩል ወጣ። 15ለአብዲዶም በደቡብ በኩል በዕቃ ቤት አንጻር ዕጣ ወጣ። 16ለሶፊምና#“ለሶፊምና” የሚለው በግሪኩ የለም። ለሖሳም በምዕራብ በኩል በዐቀበቱ መንገድ ባለው በሸለኬት በር በኩል ጥበቃ በጥበቃ ላይ ዕጣ ወጣ። 17በምሥራቅ በኩል ለየዕለቱ ስድስት፥ በሰሜን በኩል ለየዕለቱ አራት፥ በደቡብ በኩል ለየዕለቱ አራት፥ ለዕቃ ቤትም ሁለት ሁለት ነበሩ። 18በኦሳም በምዕራብ በኩል በሸለኬት በር ሦስት፥ በምሥራቅ በኩል በዐቀበቱ በር ከጥበቃ በላይ ጥበቃ በቀን ስድስት፥ በሰሜን በኩል አራት፥ በደቡብ በኩል አራት፥ በዕቃ ቤቱ በኩል ተቀባባዮች ሁለት ሁለት፥ በምዕራብ በኩል አራት በመተላለፊያውም መንገድ ተቀባባዮች ሁለት ሁለት።#ምዕ. 26 ቁጥር 18 በዕብ. የተለየ ነው። 19ከቆሬና ከሜራሪ ልጆች የነበሩ የበረኞች ሰሞን ይህች ናት።
20ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም#ዕብ. “ከሌዋውያንም አኪያ” ይላል። በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሹመው ነበር። 21የለአዳን ልጆች፤ ለለአዳን የሆኑ የጌድሶናውያን ልጆች፥ ለጌድሶናዊው ለለአዳን የሆኑ፥ የአባቶች ቤቶች አለቆች ይሔኤሊ፤ 22የይሔኤሊ ልጆች፤ በእግዚአብሔርም ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብት ላይ የነበሩ ዜቶም፥ ወንድሙም ኢዮኤል ነበረ። 23ከእንበረማውያን፥ ከይስዓራውያን፥ ከኬብሮናውያን፥ ከዑዝኤላውያን፤ 24የሙሴ ልጅ የጌርሳም ልጅ ሱባኤል በቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር። 25ወንድሞቹም፤ ከአልዓዛር ልጁ ረዓብያ፥ ልጁም የሳያ፥ ልጁም ኢዮራም፥ ልጁም ዝክሪ፥ ልጁም ሰሎሚት ነበሩ። 26ይህ ሰሎሚትና ወንድሞቹ፥ ንጉሡ ዳዊትና የአባቶች ቤቶች አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች፥ የሠራዊቱም አለቆች፥ በቀደሱት በንዋየ ቅድሳቱ ቤተ መዛግብት ሁሉ ላይ ተሹመው ነበር። 27የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሕንጻ ወደ ኋላ እንዳይል ዳዊት ከየሀገሩ በማረካቸውና በሰበሰባቸው በቀደሳቸውም ላይ የተሾሙ ናቸው። 28ነቢዩ ሳሙኤል፥ የቂስም ልጅ ሳኦል፥ የኔርም ልጅ አበኔር፥ የሶርህያም ልጅ ኢዮአብ የቀደሱት#“የቀደሱት” ማለት ለይተው የሰጡት ማለት ነው። የእግዚአብሔር ንዋየ ቅድሳት ሁሉ ከሰሎሚትና ከወንድሞቹ እጅ በታች ነበረ።
29ከይሰዓራውያን ከናንያና ልጆቹ ጻፎችና ፈራጆች ይሆኑ ዘንድ በውጭው ሥራ በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። 30ከኬብሮናውያን ሐሳብያና ወንድሞቹ፥ ጽኑዓን የነበሩት ሺህ ሰባት መቶ ሰዎች፥ ለእግዚአብሔር ሥራ ሁሉ፥ ለንጉሡም አገልግሎት በዮርዳኖስ ማዶ በምዕራብ በኩል ባለው በእስራኤል ላይ ተሾመው ነበር። 31ከኬብሮናውያንም እንደ አባቶች ቤቶች ትውልዶች የኬብሮናውያን አለቃ ኤርያስ ነበረ። ዳዊት በነገሠ በአርባኛው ዓመት ይፈልጉአቸው ነበረ፤ በእነርሱም መካከል በገለዓድ ኢያዜር ጽኑዓን ኀያላን ሰዎች ተገኙ፤ 32ወንድሞቹም ጽኑዓን የነበሩት የአባቶች ቤቶች አለቆች ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ነበሩ። ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ቃል ሁሉና በንጉሡ ትእዛዝ ሁሉ በሮቤላውያንና በጋዳውያን፥ በምናሴም ነገድ እኩሌታ ላይ ሹሞች አደረጋቸው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 26: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ