መጽሐፈ ጥበብ 4
4
1ልጅ ባይወልዱም እንካን የመልካም ምግባር ባለቤት መሆን፥
በእግዚአብሔር በሰውም ዘንድ እውቅና ስላለው፥
የማይሞት መታሰቢያ ማቆም ነው።
2ካገኘነው እርሱን እንከተላለን፤
ካጣነውም እንናፍቀዋለን።
ተፋልሞ ያሸንፋል፤ የአሸናፊነቱን ዘውድ ይደፋል፤
ዘላለማዊ ድልንም ይቀዳጃል።
3ነገር ግን የክፉዎች ልጆች ብዛት እርባና የለውም፤
ዲቃላዎች ስለሆኑም ሥር አይሰዱም፤
ጽኑ መሠረትም አያኖሩም።
4ለጊዜው ቅርንጨፎች ሊያበቅሉ ይችላሉ፤
መሠረታቸው የጸና ባለመሆኑ ነፋስ ያናጋቸዋል፤
በማዕበሉም ኃይል ተነቃቅለው ይጠፋሉ።
5ቅርንጫፎቻቸው በለጋነታቸው ይሰባበራል፤
ፍሬያቸው ዋጋ ቢስ፥
ያልበሰለና፥ ለምንም የማይጠቅም ይሆናል።
6ከሕግ ውጭ የተወለዱ ልጆች፥
በፍርድ ቀን የወላጆቸቸውን ክፋት ይመሰክራሉና።
የጻድቃን ዕድሜ ማጠር
7ጻድቅ ሰው ያለ ዕድሜው ቢሞትም፥ ዕረፍትን ያገኛል።
8የዕድሜ መርዘም ሽምግልናን አያስከብረውም፤
የዓመታት መብዛትም የሕይወት ትክክለኛ መለኪያ አይደለም።
9ሽበትስ የሰው ዕውቀቱ ነው፤ ሽምግልናም ያላደፈ ሕይወት ነው።
10እግዚአብሔርን ስላስደሰተ ተወደደ፤
በኃጢአተኞች መካከልም ስለሚኖር ተወሰደ።
11ክፋት ከሐሳቡ እንዳያዘናጋው፥
ተንኮልም ነፍሱን እንዳያታልላት እርሱ ተወሰደ።
12ክፋት መልካም ነገሮችን ያጠላባቸዋል፤
መቋጫ የሌለው ፍላጐትም ንጹሑን ልብ ያበላሻል።
13ፈጥኖ ፍጹም በመሆኑ ብዙ ኖሯል፤
14ነፍሱ ጌታን የምታስደስት በመሆኗ፥
ከከበባት ክፋት ፈጥና ወጣች፤
ሰዎች ግን ሁኔታዋን አልተረዱም፤
አእምሮአቸውም እውነታዋን አልተቀበለውም።
15የተመረጡት ሁሉ፥ ክብርና ምሕረት እንደሚጠብቃቸው፥
እርሱም ስለ እነርሱ እንደሚሟገት አልተከሠተለትም።
16ቋሚውን ኃጢአተኛ፥ ፍጹምነትን ፈጥኖ ያገኘ ወጣት፥
ኃጢአተኛውን ሽማግሌ ይፈርድበታል።
17እኒህ ኃጢአተኞች፥ የጠቢቡን ፍጻሜ ይመለከታሉ፤
ጌታ ለእርሱ ያሰበለትን ግን ከቶውንም አያውቁም፤
ከምንም እንዳዳነው አይረዱም።
18በንቀትም ይመለከታሉ፤ ጌታ ግን ይሥቅባቸዋል።
19ፈጥነውም ክብሩን ያጣ ሬሳ ይሆናሉ፤
በሙታንም መካከል ዘላለማዊ ማስፈራርያ ይሆናሉ።
እርሱ ይሰባብራቸዋል፤
በጭንቅላታቸው ያሽቀነጥራቸዋል፤
እነርሱም ይደነዝዛሉ።
ከመሠረታቸው ያናጋቸዋል፤
ወና ይሆናሉ፤ ኀዘን ይነግሥባቸዋል፤
መታሰቢያቸውም ሁሉ ይጠፋል።
ክፉዎች ሲፈረድባቸው፥
20ኃጢአታቸው ከተቆጠረ በኋላ፥
በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤
ክፉ ሥራዎቻቸውም ሊከሷቸው በፊታቸው ይቆማሉ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጥበብ 4: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ
መጽሐፈ ጥበብ 4
4
1ልጅ ባይወልዱም እንካን የመልካም ምግባር ባለቤት መሆን፥
በእግዚአብሔር በሰውም ዘንድ እውቅና ስላለው፥
የማይሞት መታሰቢያ ማቆም ነው።
2ካገኘነው እርሱን እንከተላለን፤
ካጣነውም እንናፍቀዋለን።
ተፋልሞ ያሸንፋል፤ የአሸናፊነቱን ዘውድ ይደፋል፤
ዘላለማዊ ድልንም ይቀዳጃል።
3ነገር ግን የክፉዎች ልጆች ብዛት እርባና የለውም፤
ዲቃላዎች ስለሆኑም ሥር አይሰዱም፤
ጽኑ መሠረትም አያኖሩም።
4ለጊዜው ቅርንጨፎች ሊያበቅሉ ይችላሉ፤
መሠረታቸው የጸና ባለመሆኑ ነፋስ ያናጋቸዋል፤
በማዕበሉም ኃይል ተነቃቅለው ይጠፋሉ።
5ቅርንጫፎቻቸው በለጋነታቸው ይሰባበራል፤
ፍሬያቸው ዋጋ ቢስ፥
ያልበሰለና፥ ለምንም የማይጠቅም ይሆናል።
6ከሕግ ውጭ የተወለዱ ልጆች፥
በፍርድ ቀን የወላጆቸቸውን ክፋት ይመሰክራሉና።
የጻድቃን ዕድሜ ማጠር
7ጻድቅ ሰው ያለ ዕድሜው ቢሞትም፥ ዕረፍትን ያገኛል።
8የዕድሜ መርዘም ሽምግልናን አያስከብረውም፤
የዓመታት መብዛትም የሕይወት ትክክለኛ መለኪያ አይደለም።
9ሽበትስ የሰው ዕውቀቱ ነው፤ ሽምግልናም ያላደፈ ሕይወት ነው።
10እግዚአብሔርን ስላስደሰተ ተወደደ፤
በኃጢአተኞች መካከልም ስለሚኖር ተወሰደ።
11ክፋት ከሐሳቡ እንዳያዘናጋው፥
ተንኮልም ነፍሱን እንዳያታልላት እርሱ ተወሰደ።
12ክፋት መልካም ነገሮችን ያጠላባቸዋል፤
መቋጫ የሌለው ፍላጐትም ንጹሑን ልብ ያበላሻል።
13ፈጥኖ ፍጹም በመሆኑ ብዙ ኖሯል፤
14ነፍሱ ጌታን የምታስደስት በመሆኗ፥
ከከበባት ክፋት ፈጥና ወጣች፤
ሰዎች ግን ሁኔታዋን አልተረዱም፤
አእምሮአቸውም እውነታዋን አልተቀበለውም።
15የተመረጡት ሁሉ፥ ክብርና ምሕረት እንደሚጠብቃቸው፥
እርሱም ስለ እነርሱ እንደሚሟገት አልተከሠተለትም።
16ቋሚውን ኃጢአተኛ፥ ፍጹምነትን ፈጥኖ ያገኘ ወጣት፥
ኃጢአተኛውን ሽማግሌ ይፈርድበታል።
17እኒህ ኃጢአተኞች፥ የጠቢቡን ፍጻሜ ይመለከታሉ፤
ጌታ ለእርሱ ያሰበለትን ግን ከቶውንም አያውቁም፤
ከምንም እንዳዳነው አይረዱም።
18በንቀትም ይመለከታሉ፤ ጌታ ግን ይሥቅባቸዋል።
19ፈጥነውም ክብሩን ያጣ ሬሳ ይሆናሉ፤
በሙታንም መካከል ዘላለማዊ ማስፈራርያ ይሆናሉ።
እርሱ ይሰባብራቸዋል፤
በጭንቅላታቸው ያሽቀነጥራቸዋል፤
እነርሱም ይደነዝዛሉ።
ከመሠረታቸው ያናጋቸዋል፤
ወና ይሆናሉ፤ ኀዘን ይነግሥባቸዋል፤
መታሰቢያቸውም ሁሉ ይጠፋል።
ክፉዎች ሲፈረድባቸው፥
20ኃጢአታቸው ከተቆጠረ በኋላ፥
በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤
ክፉ ሥራዎቻቸውም ሊከሷቸው በፊታቸው ይቆማሉ።