መጽሐፈ ጥበብ 16
16
ሁለተኛው ተቃርኖ፥ ዕንቁራሪቶችና ድርጭቶች
1በዚህም የተነሣ በተመሳሳይ ፍጥነቶች መቀጣታቸው፥
በተባይም መንጋ መሠቃየታቸው ተገቢ ነው።
2 #
ዘፀ. 16፥11-13፤ ዘኍ. 11፥31፤32። ከዚህ ቅጣት በተቃራኒ ለሕዝቦችህ ደግነትን አደረግህ፤
ልባቸውን አስታገስህ፤ ጣፋጭ የሆኑት ድርጭቶችም በምግብነት ሰጠሃቸው።
3ግብጻውያኑ ግን በእነርሱ ላይ የተላኩት ፍጥረታት ስለ አስጠሉዋቸው፥
እጅግ ቢራቡም የምግብ ፍላጐታቸውን ጨርሰው አጡ፤
ያንተ ሕዝቦች ግን ጥቂት ከተቸገሩ በኋላ ለየት ያለ ጣፋጭ ምግብ አገኙ።
4የቀድሞ ጨቋኞች የማያባራ ችግር ይወድቅባቸው ዘንድ አይቀርም፤
ጠላቶቻቸው ምን ያህል እንደተሠቃዩ ማየት ላንተ ሕዝቦች በቂያቸው ነው።
ሶስተኛው ተቃርኖ፥ አንበጦችና የነሐስ እባባ
5 #
ዘኍ. 21፥6-9። አራዊቱ ሕዝብህን በአስፈሪ ቁጣ በወረሯቸው ጊዜ፥
በሚጥመለመሉ እባቦች እየተነደፉ በሚያልቁበት ወቅት፥
ቅጣትህ እስከ መጨረሻው አልዘለቀም።
6ማስጠንቀቂያ ይሆናቸው ዘንድ፥ ለአጭር ጊዜ ተሠቃዩ፥
የሕግህን ትእዛዝ የሚያስታውስ የድኀንነት ምልክት ሆናቸው፤
7ወደ ነሐሱ እባብ የሚያይ ሁሉ ይድናል፤
መዳንን የሚያገኘው ግን ባየው ነገር ሳይሆን የሁሉም አዳኝ በሆንከው ባንተ ነው።
8ይህን በማድረግህም ከክፉ ነገር ሁሉ የምታድን አንተ መሆንህን ጠላቶቻችን እንዲገነዘቡ አደረገህ።
9ለእነርሱ የአምበጦችና የዝንቦች ንክሻ የሚገድል ነበር፤
ሕይወታቸውንም ለማዳን ፈውስ አልተገኘም፤
በእነኚህ ፍጥረታት ሊቀጡ ይገባቸዋልና።
10ያንተ ልጆች ግን የመርዘኞች አበቦች ጥርሶች እንኳ ሊጥሏቸው አልቻሉም፤
ይህም የሆነው በምሕረትህ ረዳትነት በመዳናቸው ነው።
11አንድ ንድፊያ፥ ፈጥኖ ይድናል፤ ቃልህን ግን እንዳይዘነጉ ያደርጋቸዋል፤
በመርሳት ባሕር ሰጥመው ደግነትህ እንዳይጓደልባቸው ያነቃቃቸዋል።
12ጌታ ሆይ ሥርም ሆነ መጠቅለያ አላዳናቸውም፥
ሁሉን የሚያድነው ቃልህ እንጂ።
13በሕይወትና በሞት ላይ ሥልጣን ያለህ አንተ ነህ፤
ወደ ሲኦል ታወርዳለህ፤ ከሲኦልም ታወጣለህ።
14ከጥላቻ የተነሣ ሰው ሊገድል ይችላል፤
የሄደውን መንፈስ ወይም ሲኦል የተረከበቻትን ነፍስ ግን ፈጽሞ ሊመልስ አይችልም።
አራተኛው ተቃርኖ፥ በረዶና መና
15ከእጅህ ማምለጥ ከቶ አይቻልም፤
16አንተን አናውቅም ያሉ ከሐዲዎች፥ በጠንካራው ክንድህ ተመቱ፤
ያልተለመደ ዝናብና በረዶ ወረደባቸው፤ የማያባራ ዶፍ አጥለቀለቃቸው፤ እሳትም በላቸው።
17ከሁሉም የሚያስደንቀው ደግሞ ሁሉን በሚያጠፋው ውሃ ውስጥ
እሳቱ እጅጉን አስፈሪ ሆነ፤ ሁሉም ለጻድቃን ይዋጋልና።
18ከሐዲዎቹን ለማጥፋት የተላኩትን እንስሶች አብሮ እንዳይደመስስ ባንድ ወቅት እሳቱ በረድ ይላል፤
እነርሱም ይህን ባዩ ጊዜ የእግዚአብሔር ፍርድ እንዳልተዋቸው ይረዳሉ፤
19በሌላ ጊዜ ደግሞ፥ ከተረገመችው ምድር የተገኘውን ፍሬ ለማጥፋት፥
በውሃው መሐከል ከእሳት የበለጠ ይንበለበላል።
20 #
ዘፀ. 16፥1-36። ለሕዝብህ ያደረግኸው ግን እንደምን የተለየ ነው
የመላእክትን ምግብ ሰጠኻቸው፤
ሁሉንም የሚያስደስት፥ ጣዕሙም ለሁሉም የሚስማማውን
የሰማይ መና ያለመሰልቸት አቀረብክላቸው።
21ለልጆችህ ያቀረብኸላቸው ልዩ ምግብ፥ ለእነርሱ ያለህን ፍቅር ያሳያል፤
የያንዳንዱን ሰው ፍላጐት ለማርካት የምግቡ ጣዕምም እንደ በላተኛው ይቀያየር ነበር።
22ውርጭና ብርድ እሳቱን ተቋቁመው፥ ሳይሟሙ ቀሩ፤
ይህ የሆነው የጠላቶቻቸውን መክር ለማጥፋት፥
እሳት በበረዶ ውስጥ እንደሚነድ፥
በዝናብም ውስጥ ቦግ ብሎ እንደሚቀጣጠል ለእነርሱ ለማሳየት ነው፤
23በሌላ በኩል ደግሞ ጻድቃኑን ለመመገብ ሲል፥
እሳት ብርታቱን እንኳን ይዘነጋል።
24ፍጡርህ ያንተ የፈጣሪው አገልጋይ ነውና፥
ኃጥአተኛውን ለመቅጣት ይወጠራል፤
አንተን ለሚያምኑት ሲል ደግሞ ይላላል።
25ሁሉንም ለመሆን በመለዋወጥ፥ የተቸገሩት ሰዎች በሚስማማቸው መልክ በመቅረብ፥
እነርሱን ለመመገብ ያሳየኸውን ችሮታ ተቀብለው የታዘዙልህ ለዚህ ነው።
26ጌታ ሆይ ይህን የተመለከቱ የተወደዱ ልጆችህም
ለሰው ምግብ የሚሆነው እህል ሳይሆን
ባንተ የሚያምኑትን ሁሉ የሚጠብቀው ቃልህ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ አደረግህ።
27እሳት ያላጠፋው፥ ባንዲት የፀሐይ ጨረር የቀለጠውም፥
28አንተን ለማመስገን ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት መነሣትና
ጎኅም ሳይቀድ አንተን ማግኘት እንዳለብን ለማሳየት ነው።
29የምስጋና ቢሱ ተስፋ ግን እንደ ክረምት ውርጭ ይሟሟል፤
እንደማይጠቅም ውሃም ይፈሳል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጥበብ 16: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ