መጽሐፈ ጦቢት 12
12
ራእይ
1የሰርጉ በዓል በተፈጸመ ጊዜ ጦቢት ልጁን ጦብያን ጠርቶ “ልጄ አብሮህ ለሄደው ሰው ደሞዙን ክፈለው፥ ሌላም ነገር ጨምርለት” አለው። 2ጦብያም እንዲህ አለው “አባቴ ምን ያህል ልስጠው? ከእኔ ጋር አብሮ ይዞት ከመጣው ገንዘብ ሁሉ ግማሹን ብሰጠውም እንኳን ምንም አይጐዳኝም፥ 3እሱ እኔን በደህና መልሶ አመጣኝ፥ ሚስቴን አዳነ፥ ገንዘቡን አመጣ፥ አንተንም ፈወሰ፥ ይህን ሁሉ ካደረገ በኋላ ታዲያ ምን ያህል ልስጠው?” 4ጦቢትም “ልጄ ካመጣው ሁሉ ግማሹን መውሰድ ይገባዋል” አለው። 5ጦብያም ጠራውና “ካመጣኸው ገንዘብ ሁሉ ግማሹን ውሰድና በሰላም ሂድ።” አለው። 6በዚያን ጊዜ ሩፋኤል ሁለቱንም ለብቻቸው ገለል አደረገና እንዲህ አላቸው፦ “እግዚአብሔርን ባርኩ፥ ያደረገላችሁንም በሕያዋን ሁሉ ፊት ምስጋናውን አውሩ፥ ስሙንም ባርኩ፥ አመስግኑም። የእግዚአብሔርን ሥራ ለሰዎች ሁሉ በሚገባ አስታወቁ፥ እሱን ከማመስገን ቸል አትበሉ። 7የንጉሥን ምሥጢር ደብቆ መያዝ መልካም ነው፥ የእግዚአብሔርን ሥራዎች ግን መግለጥና መናገር ያስፈልጋል፥ መልካምን አድርጉ፥ ክፉም አይደርስባችሁም። 8#ሲራ. 29፥8-13።ጸሎት ከጾም ጋር፥ ምጽዋትም ከጽድቅ ጋር፥ በተንኰል ከመበልፀግ የበለጡ ናቸው። ወርቅን ከመሰብሰብ ምጽዋት መስጠት ይበልጣል። 9#ምሳ. 11፥4፤ ዳን. 4፥27፤ ሲራ. 3፥30።ምጽዋት ከሞት ያድናል፥ ከሁሉም ዓይነት ኃጢአት ያነጻል። ምጽዋት የሚሰጡ ሙሉ ሕይወት ይኖራቸዋል። 10ኃጢአትንና ክፋትን የሚያደርጉ የገዛ ራሳቸው ጠላቶች ናቸው። 11አሁን እውነቱን ሁሉ እነግራችኋለሁ፥ ምንም አልደብቃችሁም፥ የንጉሥን ምስጢር ደብቆ መያዝ፥ የእግዚአብሔርን ሥራዎች ግን በግልጽ መናገር መልካም ነው ብዬ ነግሬአችኋለሁ። 12#ኢዮብ 33፥23፤24፤ የሐዋ. 10፥4፤ ራእ. 8፥3፤4።አንተና ሣራ በጸሎት ላይ በነበራችሁ ጊዜ ጸሎታችሁን በጌታ ክብር ፊት ያቀረብሁና ያነበብሁ እኔ ነኝ፥ አንተም የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ስትቀብር እንዲሁ። 13ምንም ሳታመነታ የሞተውን ሰው ሬሳ ለመቅበር ከማዕድ ትተህ በተነሣህጊዜ በዚያን ሰዓት እንድፈትንህ ተላክሁ። 14በተመሳሳይ ሰዓትም እግዚአብሔር አንተንና የልጅህን ሚስት ሣራን እንድፈውስ ላከኝ፤ 15#ዘካ. 4፥10፤ ሉቃ. 1፥19፤ ራእ. 8፥2።በጌታ ክብር ፊት ከሚገቡትና ከሚቆሙት፥ ከሰባቱ መላእክት አንዱ እኔ ሩፋኤል ነኝ።” 16ሁለቱም በጣም ደንግጠው በፍርሃት እየተንቀጠቀጡ በመሬት ላይ በግንባራቸው ተደፉ። 17እሱ ግን እንዲህ አላቸው፦ “አትፍሩ፥ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን፥ ዘለዓለም እግዚአብሔርን ባርኩት፤ 18ከእናንተ ጋር በነበርሁበት ጊዜ፥ ወደ እናንተ የመጣሁት በእግዚአብሔር ፈቃድ እንጂ በራሴ አይደለም፤ በሕይወት ዘመናችሁ ሁሉ መባረክ የሚገባችሁ እሱን ነው፥ ማመስገን የሚገባችሁ እሱን ነው። 19ስበላ ያያችሁኝ ይመስላችኋል፥ ያ ግን እይታ ብቻ ነው። 20አሁምን ከምድር ተነሱ እግዚአብሔርንም እወቁ። ወደ ላከኝ ወደ እርሱ እወጣለሁ። የሆነውን ነገር ሁሉ ጻፉት።” ወደ ላይም ወጣ። 21ከዚያም በኋላ ተነሱ፥ ሊያዩትም አልቻሉም። እግዚአብሔርን በዝማሬ አመሰገኑ፥ ታላላቅ ነገሮችን ስላደረገላቸውና የእግዚአብሔር መልአክ ስለታያቸው አመሰገኑት።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጦቢት 12: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ