መጽሐፈ ጦቢት 11
11
የጦቢት ዐይን በራ
1ከነነዌ ትይዩ ወደምትገኘው ወደ ካሠሪን ከተማ በደረሱ ጊዜ 2ሩፋኤል ጦብያን “አባትህን በምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደተውነው ታውቃለህ፤ 3ስለዚህ እኛ ከሚስትህ በፊት ቀድመን እንሂድና እነሱ እስኪመጡ ድረስ ቤቱን እናዘጋጅ” አለው። 4ሁለቱም አብረው ሄዱ፤ ሩፋኤል ጦብያን “ሐሞቱን በእጅህ ያዘው” አለው፤ ውሻውም ተከተላቸው። 5ሐና ልጇ የሚመጣበትን መንገድ እየተመለከተች ተቀምጣ ነበር። 6ልጇ ሲመጣ አየችና አባቱን “ያውልህ ልጅህ አብሮት ከሄደው ሰው ጋር እየመጣ ነው” አለችው። 7ሩፋኤል ጦብያን ወደ አባቱ ከመድረሱ በፊት እንዲህ አለው “የአባትህ ዐይኖች እንደሚከፈቱ አውቃለሁ፤ 8የዓሣውን ሐሞት በዐይኖቹ ላይ ቀባው፥ መድኀኒቱ የዐይኖቹን ነጥቦች እንዲወድቁ ያደርገዋል፥ የአባትህ ብርሃንን ያያል እንጂ ከአሁን በኋላ ዕውር አይሆንም።” 9ሐና ሮጣ በልጇ አንገት ላይ ተጠምጥማ “ልጄ አየሁህ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ግድ የለም ልሙት።” አለችው፤ ታለቅስም ጀመር። 10ጦቢት ተነስቶ እየተደነቃቀፈ ከግቢው በር ወጣ። ጦብያም ወደ እርሱ ሄደ፥ 11የዓሣውን ሐሞት በእጁ እንደ ያዘ፥ ጠበቅ አድርጎ ይዞ በዐይኖቹ ላይ እፍ አለበትና “በርታ አባቴ” አለው። በዚህም ዓይነት መድኃኒቱን አደረገለት። ለጥቂትም ጊዜ በዛ ተወው። 12#የሐዋ. 9፥18።ከዛ በኋላ በሁለት እጆቹ ከዐይኖቹ ጥግ ላይ ስስ ቆዳ ቀረፈለት። 13በዚያን ጊዜ አባቱ በአንገቱ ላይ ተጠመጠመ፥ 14አለቀሰ። “የዓይኔ ብርሃን ልጄ አየሁህ” አለ። ቀጥሎም እንዲህ አለ “እግዚአብሔር ይባረክ፤ ታላቅ ስሙ ይባረክ፤ ቅዱሳን መላእክት ሁሉ ይባረኩ፤ ታላቅ ስሙ ለዘለዓለም የተባረከ ይሁን፤ መላእክት ሁሉ ለዘለዓለም የተመሰገኑ ይሁኑ፤ 15በመከራ ቀጥቶኝ ነበር፥ ምሕረት አደርገልኝ፥ አሁን ልጄን ጦብያን አየሁት።” ጦብያ ደስ ብሎት በታላቅ ድምፅ እግዚአብሔርን እያመሰገነ ወደ ቤት ገባ። ሁሉንም ነገር ማለትም መንገዱ እንዴት እንደ ተቃናለት፥ ገንዘቡንም ተቀብሎ እንደመጣ፥ የራጉኤልን ልጅ ሣራን እንዴት እንደአገባት በነነዌ ከተማ አጠገብ እንደደረሰችና በቅርብ እንደምትምጣ ለአባቱ ተረከለት። 16ጦቢት ደስ ብሎት እግዚአብሔርን እያመሰገነ የልጁን ሚስት ለመቀበል ወደ ነነዌ በር ወጣ። የነነዌ ሰዎች ጦቢትን ማንም ሳይመራው ሲራመድና ሲዘዋዋር ባዩት ጊዜ ተደነቁ። 17ጦቢትም እግዚአብሔር እንደራራለትና ዐይኖቹን እንደ ከፈተለት በእነሱ ፊት ይናገር ነበር። በዚያን ጊዜ ጦቢት ከልጁ ከጦብያ ሚስት ከሣራ ጋር ተገናኘ፥ እንዲህም ብሎ ባረካት “ልጄ እንኳን ደኀና መጣሽ፥ ልጄ ወደኛ ያመጣሽ አምላክሽ የተባረከ ይሁን፥ አባትሽና እናትሽ የተባረኩ ይሁኑ፥ የእኔ ልጅ ጦብያም የተባረከ ይሁን፥ አንቺም ልጄ የተባረክሽ ሁኚ፥ በደስታና በበረከት ቤትሽ እንኳን በደኀና መጣሽ፥ ግቢ ልጄ።” በዚያን ቀን በነነዌ በሚኖሩ አይሁዳውያን መካከል ደስታ ሆነ። 18የጦቢት የአጎቱ ልጆች አሂካርና ናዳብም የጦቢትን ደስታ ለመጋራት መጡ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ጦቢት 11: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ