ወደ ቲቶ 1:5-10

ወደ ቲቶ 1:5-10 መቅካእኤ

የተቀረውን ሥራ እንድታቃናና በየከተማው እኔ እንዳዘዝሁህ ሽማግሌዎችን እንድትሾም፥ አንተን በዚህ ምክንያት በቀርጤስ ተውሁህ፤ ነቀፋ የሌለበትና የአንዲት ሚስት ባል የሆነ፥ በመዳራትም ወይም ባለመታዘዝ የማይከሰሱ አማኝ ልጆች ያሉት ማንም ሰው ቢኖር፥ ሹመው። ኤጲስ ቆጶስ እንደ እግዚአብሔር መጋቢ ነቀፋ የሌለበት ሊሆን ይገባዋል፤ የማይኮራ፥ የማይቆጣ፥ የማይሰክር፥ ጠበኛ ያልሆነ፥ ለገንዘብ የማይስገበገብ፥ ነገር ግን እንግዳ ተቀባይ፥ በጎ የሆነውን ነገር የሚወድ፥ ጠንቃቃ፥ ጻድቅ፥ ቅዱስ፥ ራሱን የሚቈጣጠር ይሁን፤ እውነተኛውንም ትምህርት ለመምከርና ተቃዋሚዎቹን ለመገሠጽ እንዲችል፥ እንደተማረው በታመነ ቃል ይጽና። የማይታዘዙና ከንቱ ነገርን የሚያወሩ የሚያታልሉ በተለይም ከተገረዙት ወገን የሆኑ ብዙ ሰዎች አሉና፤