መጽሐፈ ሲራክ 40
40
የሰው ምስኪንነት
1የመከራ ዕጣ ለሰዎች ተፈጥሯል፤ በአዳም ልጆች ላይ ከባድ ቀንበር ተጭኗል፤ ከእናታቸው ማሕፀን ከወጡበት ዕለት ጀምሮ፥ ወደ ሁሉም እናት እስኪመለሱ ድረሰ፥ እንዲሁ ይኖራሉ። 2እነርሱን የሚያስጨንቅ፥ ልባቸውንም የሚያሸብር፥ ዕለተ ሞታቸው ነው። 3በከበረ ዙፋን ላይ ከተቀመጠው ሰው ጀምሮ፥ በትቢያና በአመድ ላይ እስከወደቀው ምስኪን ድረስ፥ 4ከፋይ ከለበሰው፥ ዘውድ ከደፋው ጀምሮ፥ ማቅ እስከለበሰው ድረስ ቁጣና ቅናት፥ ብጥብጥና ሁከት፥ የሞት ፍርሃት፥ ምቀኝነት፥ ግጭትም በሰፊው ነግሠዋል። 5ሌት እንኳ ባልጋው ላይ ባረፈ ጊዜ፥ መኝታው ጭንቀቱን ያባብስበታል። 6ለማረፍ እንደተጋደመ ብዙም ሳይቆይ፥ እንደ ቀኑ ሁሉ በእንቅልፍ ልቡም ቅዠቶች ያስጨንቁታል፤ ከጦርነት እንዳመለጠ፥ 7በማምለጥም ላይ ሳለ እንደነቃና የሚያስፈራም ነገር ባለ መኖሩ የተደነቀ ሰውን ይመስላል። 8ለሰውና ለእንስሳት፥ ለሁሉም ፍጥረታት፥ ሰባት ጊዜ እጥፍ ደግሞ ለኃጢአአተኞች፥ 9ሞትና ደም፥ ፀብና ሰይፍ፥ ጥፋትና ረሃብ፥ መከራና መዓት ይጠብቋችኋል። 10እነኚህ ሁሉ የተፈጠሩት ለኃጥአን ነው፤ የጥፋት ውሃ የወረደውም በእነርሱ ምክንያት ነው። 11ከምድር የተገኘ ሁሉ ወደ ምድር፥ ከውሃም የተገኘ ወደ ባሕር ይመለሳል።
ልዩ ልዩ ምሳሌዎች
12ጉቦና ፍትሕ ማጓደል ሁሉ ይወገዳሉ፤ መልካም እምነት ግን ለዘለዓለም ይኖራል። 13ያለ አግባብ የተገኘ ሃብት እንደ ወራጅ ውሃ፥ የዝናቡን መምጣት እንደሚያበስርም ነጐድጓድ ብልጭ ብሎ ይጠፋል። 14እጁን ሲዘረጋ ይደሰታል፤ ኃጢአተኞችም ያኔውኑ በቅጽበት ይጠፋሉ። 15የክፉ ሰዎች ቀንበጦች፥ ቅርንጫፎቻቸው አይበዙም፤ የተበከሉ ሥሮች የሚያጋጥማቸው ጠንካራ ዓለት ብቻ ነው። 16በወንዝ ጠርዝ ላይና በሐይቅ ዳር የሚበቅል ሸምበቆ፥ ከሚነቅሉት ተክሎች የመጀመሪያው ነው። 17ቸርነት ዋነኛው የምርቃት ገነት ነው፤ ምጽዋትም ዘለለማዊ ነው። 18የግል መተዳደሪያ ላለውና ጠንክሮ ለሚሠራ ሰው፥ ሕይወት አስደሳች ነች። ሀብት ያገኘ ደግሞ ከሁለቱም የተሻለ ነው። 19ልጆች መውለድና ከተማን መቆርቆር ስምን ያስጠራል፤ ንጹሕ ሚስት ግን ከሁለቱም የከበረች ነች። 20የወይን ጠጅና ሙዚቃ ልብን ያስደስታሉ፤ የጥበብ ፍቅር ግን ከሁሉም ይልቃል። 21ዋሽንትና በገና መዝሙር ያጣፍጣሉ፤ ለዛ ያለው ድምፅ ግን ከሁሉም ይበልጣል። 22ዐይን ግርማንና ውበትን ይናፍቃል፤ ከሁለቱም የተሻለው ግን የፀደይን ልምላሜ መመልከት ነው። 23ወዳጅም ሆነ ጓደኛ ሲገኝ ያስደስታል፤ የባልና የሚስት መገኘት ግን የበለጠ ደስ ያሰኛል። 24ወንድሞችና ደጋፊዎች ለመከራ ይደርሳሉ፤ ነገር ግን ምጽዋት ይበልጥ አዳኝ ነው። 25ወርቅና ብር ጠንክረህ እንድትቆም ያደርጋሉ፤ ከሁለቱም የተሻለው ደግሞ መልካም ምክር ነው። 26ብርና ኃይል ደንዳና ልብን ይፈጥራሉ፤ እግዚአብሔርን መፍራት ግን ከሁሉም ይልቃል፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ አንዳች አያጣም፤ የሌሎችንም ድጋፍ አይሻም። 27እግዚአብሔርን መፍራት የምርቃት ገነት ነው፤ ከታላቅ ክብርም ይልቅ ያድናል።
መቀላወጥ
28ልጄ ሆይ! ከሌሎች በመቀላወጥ አትኑር፤ ቀላዋጭ ከመሆን መሞት ይመረጣል። 29የሌላውን ሰው ማዕድ በመቀላወጥ የሚገፋ ሕይወት፥ ከቶውንም ሕይወት አይባልም፤ የሌሎች ምግብ ጉሮሮን ያሳድፋል፤ ጥበበኛ የሆነና መልካም አስተዳደግ ያለው ሰው ይህን አያደርግም። 30የቀላዋጩ ቃል ሲሰሙት ይጣፍጣል፤ በሆዱ ውስጥ ግን እሳት ይነዳል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 40: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ