መጽሐፈ ሲራክ 39
39
ጸሐፍት
1የልዑል እግዚአብሔርን ሕግ የሚያጠናና የሚመረምር፥ እንዲህ አይደለም፤ የጥንታውያኑን ሰዎች ጥበብ ያጠናል፥ ትንቢቶችንም ይመረምራል። 2የዝነኛ ሰዎች ንግግሮችን በወጉ ይይዛል፥ ምሳሌችን ሁሉ ጠንቅቆ ያውቃል። 3የምሳሌዎቹን ምሥጢራት ይመረምራል፥ እንቆቅልሻቸውንም ይፈታል። 4ልዑላኑን ያገለግላል፥ መሪዎች ባሉበትም አይጠፋም። ወደ ውጭ ሀገሮችም ይጓዛል፥ የሰውን ደግነትና ክፋት ጠንቅቆ ያውቃል። 5ንጋት ላይ በንጹሕ ልቡ ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሔር ፊቱን ይመልሳል፤ በልዑል እግዚአብሔር ፊት ልመናውን ያቀርባል፥ አፉንም የሚያሟሸው በጸሎት ነው፥ ስለ ኃጢአቱም ይቅርታን ይለምናል። 6የታላቁ እግዚአብሔር ፈቃድ ይህ ከሆነ፤ እርሱ በእውቀት መንፈስ ይሞላል፥ የጥበብን ቃላት ያዘንበል፥ በጸሎቱም እግዚአብሔርን ያመሰግናል። 7በዓላማና በትምህርት ትክክለኛ ሆኖ ያድጋል፤ የእግዚአብሔርን ድብቅ ምሥጢራት ጠልቆ ይመረምራል። 8የተማረውን በውል ያስመሰክራል፤ በእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ሕግም ይኩራራል። 9ብዙዎች ዕውቀቱን ያመሰግኑለታል፤ ፈጽሞ የሚረሳም አይደለም፤ መታሰቢያውም አይጠፋም፤ ከትውልድ ወደ ትውልድም ስሙ ሕያው ሆኖ ይኖራል። 10ሀገሮች ጥበቡን ያደንቃሉ፤ በጉባኤ ፊት ይመሰገናል። 11ዕድሜ ከሰጠው ስሙ ከሌሎች ሺህ ስሞች የበለጠ የተከበረ ይሆናል፥ ቢሞትም ይኸው ይበቃዋል።
እግዚአብሔርን የማመስገን ጥሪ
12ቀሪዎቹ ሐሳቦቼን እነሆ አቀርባለሁ፥ ሞልታ እንደምትታየው ጨረቃ ሙሉ ሆኛለሁ! 13ጻድቃን ልጆቼ ሆይ ስሙኝ! በወንዝ ዳር እንደ በቀለ ጽጌሬዳ እናንተም አብቡ። 14የዕጣንን መልካም ሽታ ይስጣችሁ፥ እንደ ነጭ አበባ አብቡ፥ መዓዛችሁ ዙሪያችሁን ያውድ፥ የምስጋና መዝሙር ዘምሩ፥ ስለ ሥራዎቹ ሁሉ እግዚአብሔርን ባርኩ። 15የስሙን ታላቅነት አውጁ፥ በመዝሙርና በክራር እርሱን አመስግኑ፥ ምስጋናውንም የምታዜሙት እንዲህ በማለት ነው፥ 16የእግዚአብሔር ሥራዎች ምንኛ ድንቅ ናቸው? ትዕዛዛቱም ሁሉ በጊዜአቸው ይፈጸማሉ! ይህ ምንድነው? ይህስ ለምን ተፈጸመ? ማለት አይገባህም፤ ለሁሉም ጥያቄ ጊዜ አለው። 17ቃሉን በሰማ ጊዜ ውሃው ይቆማል፤ ከፍ እያለም ይከማቻል፥ ድምፁን በሰሙ ጊዜ የውሃ ማጠራቀሚያዎች ይፈጠራሉ። 18በእርሱ ትእዛዝ የፈቀደው ሁሉ ይፈጸማል፤ ማዳን ከፈለገ የሚገታው የለም። 19የሰው ልጅ የሚሠራውን ሁሉ ያያል፤ ከዐይኖቹ ሊሠወር የሚችል ከቶ ምንም የለም። 20እይታው መጨረሻም መጀመሪያም የለውም፤ አንድም ነገር ከቶ አያስደንቀውም። 21ይህ ምንድነው? ያስ ለምን ሆነ? ማለት አይገባህም፤ ሁሉም ነገር የተፈጠረው በምክንያት ነውና። 22ምርቃቱ ደረቁን መሬት እንደ ወንዝ እንደሚያርሰው፤ እንደ ጐርፍም እንደሚያጥለቀልቀው ሁሉ፥ 23ቅጣቱም እንዲሁ ውሃን ወደ ጨው እንደቀየረ፥ ለአሕዛብ የሚሰጣቸው ውርሱ ነው። 24መንገዶቹ ሁሉ ለጻድቃን የተስተካከሉ፥ ለኃጥአን በመሰናክል የተሞሉ ናቸው። 25መልካሙ ሁሉ ለደጋጐች፥ መጥፎው ሁሉ ለክፉዎች የተፈጠረ ነው። 26ለሰው ሕይወት አስፈላጊ የሆኑ ነገሮች፥ ውሃና እሳት፥ ብረትና ጨው፥ የስንዴ ዱቄት፥ ወተትና ማር፥ የወይን ጭማቂ፥ ዘይትና ልብስ ሲሆኑ፥ 27እነኚህ ሁሉ ለጻድቃን ጥሩ፤ ለኃጢአተኞች ግን መጥፎ ናቸው። 28ለቅጣት የተፈጠሩ ነፍሳት አሉ፤ በተቆጣም ጊዜ በመቅሰፍትነት ይልካቸዋል፤ በጥፋት ቀን ኃያልነታቸውን ያሳያሉ፤ የፈጣሪያቸውንም ቁጣ ያበርዳሉ። 29እሳትና ብርድ፥ ረኀብና ሞት፥ የተፈጠሩት ለቅጣት ነው። 30የአራዊት ጥርሶች፥ ጊንጦችና እፉኝቶች፥ ኃጢአተኞችን የሚያጠፉ የበቀል ሠይፍ ናቸው። 31ትእዛዛቱን በመፈጸም ሁሉም ይደሰታሉ፤ በምድር ላይ ባስፈላጊው ጊዜ ሁሉ ዝግጁዎች ናቸው፤ ጊዜያቸው በደረሰ ጊዜም ከቃሉ አይወጡም። 32እኔም ከመነሻዬ የቆረጥኩት ለዚሁ ነው፤ የተመራመርኩት፥ የጻፍኩትም ከዚህ በመነጨ ነው። 33የእግዚአብሐር ሥራዎች ሁሉ መልካም ናቸው፤ ጊዜው በደረሰ ጊዜ አስፈላጊውን ሁሉ ይሰጣል። 34“ይኸኛው ከዚያኛው የባስ ነው” ማለት የለብህም፤ ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ ሁሉም ምንነቱን ያሳያል። 35እንግዲህ አሁን በሙሉ ልበ፥ ለዛ ባለው ድምፅ፥ የእግዚአብሔርን ስም ባርክ።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 39: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ