መጽሐፈ ሲራክ 35
35
ሕጉና መሥዋዕቶች
1ሕጉን የሚፈጽም ብዙ መባ እንዳቀረበ ይቆጠርለታል። ትእዛዛቱን የሚያከብር የኀብረት መሥዋዕቶችን ያቀርባል። 2የውለታ መላሽነት ማረጋገጫ የዱቄት መባ ነው፤ መመጽወት የምስጋና መሥዋዕት ነው። 3ከክፋት መራቅ እግዚአብሔርን ያስደስታል፤ ከበደል መታቀብ የማስተሥረያ መሥዋዕት ነው። 4በእግዚአብሔር ፊት ባዶ እጅህን አትቅረብ፤ እነኚህ ሁሉ ትእዛዛቱ ናቸውና። 5የእውነተኞች መባ መሠውያውን ግርማ ያጐናጽፈዋል፤ መዓዛውም ከልዑል እግዚአብሔር ፊት ይቀርባል። 6የጻድቃን መሥዋዕት ተቀባይነት አለው፥ መታሰቢያውም አይዘነጋም። 7በቸርነትህ እግዚአብሔርን አክብር፤ በኵራትህም ስታቀርብ አትሰስት። 8ስጦታዎችህን ስታቀርብ ከፈገግታ ጋር ይሁን፤ እሥራትህን በደስታ አቅርብ። 9#2ቆሮ. 9፥7።እግዚአብሔር እንደሰጠህ ሁሉ ለእርሱም ሰጠ፤ ይህንንም አቅምህ እንደሚፈቅድ አድርግ። 10እግዚአብሔር ለጋስ ስለሆነ ሰባት ጊዜ እጥፍ ይሰጥሃል።
መለኮታዊ ፍትሕ
11ስጦታዎችን በመማለጃነት አታቅርብ፥ እርሱ አይቀበልህምና። በቅንነት ባልቀረቡ መሥዋዕቶች ላይ እምነት አትጣል፤ 12እግዚአብሔር አድልዎን የሚያውቅ ፍጹም ዳኛ ነውና። 13ስለድሆች መጐዳት አያዳላም፤ የተጐዳውን ወገን አቤቱታም ያዳምጣል። 14የሙት ልጅ የሚያቀርቡለትን ልመና አይዘነጋም፤ የመበለቷንም መሬት ቸል አይልም። 15ለመከራው ምክንያት የሆነውን ሰው ስትከስ፥ የመበለትዋ እንባ በጉንጮችዋ አይወርድምን? 16በሙሉ ልብ የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነ ሰው ተቀባይነትን ያገኛል፤ ልመናውም እስከ ሰማይ ይደርሳል። 17የትሑት ሰው ጸሎት ደመናትን ያቋርጣል። ከፈጣሪም ዘንድ እስኪደርስ አይጽናናም። 18ልዑል እግዚአብሔር ወደ እርሱ እስካላየ ድረስ፤ ጻድቃንም ፍትሕን ካላገኙ በቀር ጸሎቱን አያቋርጥም። 19እግዚአብሔርም፥ 20ጨካኞችን ካላኮላሸ፥ በመንግስታቱ ላይ ካልተበቀለ፥ 21የግትሮችን ክምር ካልናደ፥ የበደለኞችን በትረ መንግሥት ካልሰበረ፥ 22ለሰው ሁሉ እንደ ሥራው ካልከፈለ፥ ድርጊቶቻቸውም እንደ አነሳሳቸው ዋጋ ካላገኙ፥ 23የሕዝቡን ሁናቴ መርምሮ በምሕረቱ ካላስደሰታቸው አይታገሥም። ስለ እነርሱም ሲል አይዘገይም። 24በመከራ ጊዜ የሚገኝ ምሕረት፥ በድርቅ ወቅት እንደሚታዩ የዝናብ ደመናዎች ያስደስታል።
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 35: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ