መጽሐፈ ሲራክ 33
33
1እግዚአብሐርን የሚፈራ ክፉ ነገር አያገኘውም፤ በመከራ ጊዜ እንኳ ይድናል። 2ሕጉን የሚጠላ ጠቢብ አይደለም፤ ግብዝም ሰው በማዕበል እንደሚንገላታ መርከብ ነው። 3#ዘፀ. 28፥30፤ ሲራ. 45፥10።አዋቂ ሰው በሕጉ ያምናል፤ እንደ ትንቢትም ይቀበለዋል፤ 4የምትናገረውን አዘጋጅ፤ አድማጭ ታገኛለህ፤ መልስም ከመስጠትህ በፊት መረጃዎችህን አጠናቅር። 5የሞኝ ስሜት እንደ ጋሪ እግር ነው፤ አስተሳሰቡም እንደ ቅትር ይሽከረከራል። 6ድንጉላ ፈረስ እንደ አሽሟጣጭ ወዳጅ ነው፤ ማንም ቢጋለበው ያሸካካል።
ልዩነት
7ፀሐይ በዓመቱ ባሉት ቀናት እኩል ብርሃን ብትለግስም፥ ስለምን አንድ ቀን ከሌላው የተሻለ ይሆናል? 8በዓላትንና ወቅቶችን ይለያየው ጌታ፥ እነርሱንም ለያይቷቸዋል። 9ከፊሎቹን ታላቅና የተቀደሱ፤ ሌሎቹን ደግሞ ተራ አድርጓቸዋል። 10የሰው ልጆች የተገኙት ከምድር ነው። አዳምም የተፈጠረው ከአፈር ነው። 11እግዚአብሔር በታላቅ ጥበቡ የተለያዩ አድርጓቸዋል፤ አኗኗራቸውም ለየግል ነው። 12አንዳንዶቹን ባርኳቸዋል፥ ቀድሷቸዋል፤ ወደ እርሱም አቅርቧቸዋል። ሌሎቹን ደግሞ ረግሟቸዋል፥ አዋርዷቸዋል፤ ከሥልናቸው ነቅሎ ጥሏቸዋል። 13ሸክላ ሠሪው ጭቃውን በፈለገው መልክ እንደሚቀርጸው ሁሉ፥ በፈጣሪያቸው እጅ ያሉት ሰዎችም እንዲሁ በፍርዱ መሠረት የሚገባቸውን ያገኛሉ። 14በክፋት ፊት ደግነት፥ በሞት ፊት ሕይወት እንዳለ ሁሉ፥ በጻድቁም ፊት ኃጢአተኛው ይቆማል። 15የልዑል እግዚአብሔርን ሥራዎች ብትመረምር፥ ሁሉም ጥንድና ተቃራኒ ሆነው ታገኛቸዋለህ። 16ከሁሉም መጨረሻ የመጣሁ እኔ ብሆን፥ ከወይን ቆራጮች የተረፈውነ እንደሚሰበስበው ሰው ዓይኔ ሁሉንም ይመለከት ነበር። 17በእግዚአብሔር ቡራኬ ቀድሜ ገባሁ፤ እንደ ትክክለኛው የወይን ቆራጭ፥ መጭመቂያዬንም ሞላሁ። 18የምሠራውም ለግሌ እንዳልነበር አስተውል፤ ትምህርት ለሚሹ ሁሉ እንጂ። 19የተከበራችሁ የሕዝብ መሪዎች አድመጡኝ! የጉባኤው ሰብሳቢዎችም ጆሯችሁን አውሱኝ።
ነጻነት
20በሕይወት ዘመንህ፥ ለልጅህም ሆነ ለሚስትህ፥ ለወንድምህም ሆነ ለወዳጅህ፥ ባንተ ላይ ሥልጣንን አትስጣቸው። ሐብትህንም ቢሆን ለማንም አትስጥ፤ ድንገት እንኳ ብትቆጭ፥ መልሱልኝ ብለህ መጠየቅ ይኖርብሃልና። 21በሕይወት እስካለህና እስትንፋስህ እስካልቆመች ድረስ፥ ባንተ ያዝ ዘንድ ለማንም ሥልጣንን አትስጥ። 22አንተ የእነርሱን ፊት ከምታይ፥ ልጆችህ አንተን ቢለምኑህ ይሻላል። 23በምትሠራው ሁሉ ኃላፊው አንተ ሁን፤ ክብርህንም ሳታዋርድ እለፍ። 24ሞት በላይህ ባንዣበበ ጊዜ፥ በመጨረሻዋ ሰዓት ውርስህን አከፋፍል።
አገልጋዮች
25ድርቆሽ፥ ዱላና ሸክም ለአህያ፥ እንጀራ፥ ሥርዓትና ሥራ ደግሞ ለአገልጋይ ነው። 26አገልጋይህን ከጠመድከው የአእምሮ ሰላምን ታገኛለህ፤ ሥራ ፈትቶ ከተቀመጠ ግን ነጻነቴን ይልሃል። 27ቀንበርና ልጓም አንገት ያስደፋሉ፤ ቅጣትና ሥቃዩም እንዲሁ መጥፎ አገልጋይን ያርማሉ። 28ሥራ ፈትቶ እንዳይቀመጥ አሠራው፤ ሥራ ፈትነት ተንኮልን ያስተምራል። 29ከሥራው ፈቀቅ እንዳይል አድርግ፤ አልታዘዝም ካለ እሠረው። 30ግና ማንንም ቢሆን ከሚገባው በላይ አትቅጣ፤ ፍትሕን አታዛባ። 31አገልጋይህ አንድ ብቻ ነውን? በደም ያገኘኸው ነውና እንደ ራስህ እየው። አገልጋይህ አንድ ብቻ ነውን? ራስህን እንደምትፈልገው ሁሉ፤ እርሱም ያስፈልግሃልና እንደ ወንድምህ እየው። 32በአግባቡ ባትይዘው ግን ትቶህ ይኮበልላል፤ 33በየትኛውስ መንገድ ልትፈልገው ትሄዳለህ?
Currently Selected:
መጽሐፈ ሲራክ 33: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ